የሴት ካቢኔ አባላቱ ሹመት ለፖለቲካ አመራርነት ተሳትፎ መሰረት ይጥላል

0
1221

በድሬዳዋ አስተዳደር የሚኖሩ ነዋሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ሰሞኑር በተዋቀረው የካቢኔ አባላት 50 በመቶ ሴቶች መሆናቸው ላይ አስተያየት ሰተዋል፡፡

ነዋሪዎቹ በሰጡት አስተያየት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ያቀረቡትን 20 የካቢኔ አባላት ሹመት 50 በመቶዎቹ ሴቶች መደረጉ በከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ አመራርነት ተሳትፎ እንዲኖራቸው እየተደረገ ላለው ጥረት መሰረት የሚጥል ብለዋል፡፡

አሰተያየት ሰጪዎቹ በተጨማሪም የተመረጡት የካብኔ አባላት የአገልጋይነት ስሜት ኖሯቸው ሀገራቸው የጀመረችውን ለውጥ የሚያስቀጥሉ እንዲሆኑም ሲሉ በአስተያየታቸው ተናግረዋል ፡፡

በምክር ቤቱ በፀደቀው 50 በመቶዎቹ የካቢኔ አባላት

  1. ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ———የሰላም ሚኒስትር
  2. ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረ እግዚአብሔር ———–ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር
  3. ኢንጂነር አይሻ መሐመድ———— የሀገር መከላከያ ሚኒስትር
  4. ወይዘሮ አዳነች አቤቤ———– የገቢዎች ሚኒስትር
  5. ዶ/ር ፍፁም አሰፋ————— የፕላንና ልማት ኮሚሽን ሚኒስትር
  6. ደ/ር ሂሩት ወ/ማርያም———— የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር
  7. ደ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ————–የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
  8. ወይዘሮ የዓለምፀሐይ አሰፋ———— የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር
  9. ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ———— የትራንስፖርት ሚኒስትር
  10. ደ/ር ሂሩት ካሳው————— የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር በመሆን ተሹመዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here