ለተቀዳጀነው ትክክለኛ ዴሞክራሲ ዋጋ ልንሰጥ ይገባል

0
719

የአቋም መግለጫ

ለተቀዳጀነው ትክክለኛ  ዴሞክራሲ ዋጋ ልንሰጥ ይገባል

“ዴሞክራሲ” ቃሉ ከግሪክ የመጣና የፖለቲካ ጉዳይ ሲነሳ ሁሌም አብሮ የሚነሳ ታልቅ መልዕክት ያዘለ ቃል ነው፡፡ በየጊዜው ወደ ስልጣን ሊመጡ የሚፈልጉ የፖለቶካ ፓርቲዎች የህዝብን ልብ ለመማረክና ትኩረት ለማግኘት በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ደጋግመው የሚናገሩት ቃል ነው፡፡

ይሁን እንጂ ብዙዎች በተግባር ለማሳየትና ልክ እንደ ቃሉ መሠረታዊ ትርጉም ስልጣን የህዝብስለሆነ ከህዝብ ፍላጎትና ፈቃድ ውጪ የሚደረግ የትኛውም ነገር ተቀባይነት እንደሌለው ማረጋገጥ ሲሳናቸው ይታያሉ፡፡ ምክኒያቱም ከስልጣን የሚገኘውን ጥቅም ላለማጣትና የአቅም ክፍተታቸው እንዳይነገራቸው የተለያዩ ደንብና መመሪያ በማብዛት የዜጎቻቸውን ዴሞክራሲያዊና ሰብዐዊ መብቶችን መሸራረፍ እንደ ጥሩ አማራጭ ሊጠቀሙበት ስለሚፈልጉ ነው፡፡

በሀገራችንም ባሳለፍናቸው የመንግስት ሥርዐቶች በተጨባጭ ያየነው ይህንኑ ሀቅ ነው፡፡ በዐጼዎቹ ሥርዓት ህዝብ ከየት እንደመጣ የማያውቀውን ህገ መንግሰት ራሳቸው አርቅቀውና አጽድቀው እንደ ገጸ-በረከት በማቅረብ እንደ አምላክ እንዲሰገድላቸው ላድገው ለዘውድ አገዛዛቸው ተጠቅመውበታል፡፡

 በመቀጠልም ግርግሩን በመጠቀም ወደ ስልጣን የመጣው ደርግ በነበረው ህገ-መንግስት ላይ ጥገናዊ ለውጥ ብቻ በማድረግ ለአፈናና ለጭቆና ተግባሩ እንደ ህጋዊ ሽፋን ተጠቅሞበታል፡፡ በእርግጥ የደርግ አገዛዝ ለየትኛውም ህግ የማይገዛና ህግን አፈሙዝ ያደረገ፤ በአደባባይ ህገ-መንግስትን በመጣስ ወደር የሌለው ሥርዓት ለመሆኑ ሁላችንንም የሚያግባባ ሀቅ ነው፡፡

ደርግ ጭቆና ባንገፈገፋቸው የህዝብ ልጆች የትጥቅ ትግል ከተፈረካከሰ በኋላ ህዝብን በውክልና ዴሞክራሲ ያሳተፈ ምርጥ ህገ-መንግስት ባለቤቶች ሆነን ነበር፡፡ እያደር ግን የህዝብን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በወጉ ማስተናገድ ያቃተው መንግስት በዴሞክራሲ ስም የእስር ቤትና የማሰቃያ ማዕከሎችን በመክፈት ዜጎችን ሲያሰቃይ እንደነበር ስንሰማ ሁላችንም ተገረመናል፤ ደንግጠናል፡፡

አሁን ግን በፍቅር፣ በይቅርታና በመደመር የለውጥ ጉዟችን በርካታ ያጣናቸውና ኢትዮጰያዊ ክብርን የሚያላብሱን መብቶቻችንን እየተቀዳጀን ነው፡፡ የትኛውም ዜጋ ዴሞክራሲያዊና ሰብዐዊ መብቶቹን በነጻነት በአደባባይ እየተገበረ ባለበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን፡፡ ትክከለኛው ዴሞክራሲም ህዝብ ያልተሸራረፈ መብቶቹን ፍጹም በሆነ ነጻነት ያለፍርሀት በየትኛውም ቦታ ሲተገብረው የሚታየው ድባብ ነው፡፡

ይሁን እንጂ የዴሞክራሲ ትርጉሙ ሳይገባን ቀርቶ ይሁን ወይስ ሁን ተብሎ እውነታው ባልተለየ መንገድ መብቶቻችንን የሌላውን መብት ለመጣስ ስንጠቀምበት ይስተዋላል፡፡ ይህ ድርጊት የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ ያዳክማል እንጂ ምንም ፋይዳ የለውም፡፡

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

ድሬዳዋ

07/01/2011ዓ.ም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here