ሀገር ብቻ ሳይሆን ራዕይንም ጭምር የሚረከብ ትውልድ ያስፈልጋል

0
665

       በጥላቻና በቂም በቀል ላይ ከከፈትነው መጠነ ሰፊ ዘመቻ ባልተናነሰ ደረጃ በኪራይ ሰብሳቢነት፣ በትምክህት፣ በጥበትናበሀይማኖት አክራሪነት ላይም የተጠናከረና ቀጣይነት ያለው ዘመቻ መክፈትና መረባረብ የምን ጊዜም ትኩረታችን ሊሆን ይገባል፡፡ በአመለካከትና በተግባር እዚህም እዚያም ብቅ እያሉ ተመልሰው ደግሞ የጠፉ እየመሰሉ እንደገና የሚያገረሹትን የኪራይ ሰብሳቢነት፣ የትምክህት፣ የጥበትና የሀይማኖት አክራሪነት መዋቅሮችንየመበጣጠስ ሥራ ቀጣይነቱ ትኩረት ሊሠጠው ይገባል፡፡

እነዚህንበስውርና በግልጽ እየታዩ ያሉ አመለካከቶችና ተግባራት ከመሠረታቸው ለመናድ ታስቦ በተሠራው ሥራ የታዩ ለውጦች ቢኖሩም በቂ ግን አይደለም፡፡ ተቋማዊ አደረጃጀትና አቅም መፍጠር ተችሏል፡፡ ለእነዚህ አመለካከቶችና ተግባራት የማይመች ተቋማዊ አሠራርና አደረጃጀት ከመፍጠር ጐን ለጐን  አመለካከቶቹንም ሆነ ተግባራቱን ፈፅሞ የማይሸከም ትውልድ መፍጠር ሥርዐቱን ለማስቀጠልና ውጤታማ ሥራ ለመሥራት በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ትውልድንበአመለካከት እየቀረጹ መሄዱቀጣይነት ባለው መልኩ ሀገርን በመገንባት ሥራው ጠንካራ አስተማማኝና ምቹ መደላድል ስለሚፈጥር ፋይዳው ትውልድን የሚሻገር ነው፡፡ ስለዚህ በአመለካከት ትውልድን የመቅረፅ ሥራው በትኩረት ታስቦበትና መርሀ ግብር ወጥቶለት ሳይቆራረጥ ሊኬድበት እንደሚገባ በድጋሜ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡

        እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው ተግባራትና አመለካከቶች በተያያዝነውየፍቅር፣ የአንድነትና የመደመር ጉዞ  ግስጋሴ ፊት የተደቀኑ ፈተናዎች መሆናቸውን በተደጋጋሚ ካሳለፍናቸው ተሞክሮዎች በተግባር ለመመልከት ችለናል፡፡ እነዚህን ፈተናዎች በብቃት ለመወጣትአምርሮ የህግ የበላይነትን ማስከበሩ እንዳለ ሆኖ ትውልድን ማንቃት ማስተማርና እነዚህን አመለካከቶች የማይሸከምና ጽኑ አቋም ያለው ትውልድ መገንባት ይገባል፡፡

        የህገ መንግስታችንን መሠረታዊ መርሆዎች በውል የተረዳና  ህገ-መንግስታችንንና ህገ-መንግስታዊ ስርዓታችንን ያለማንም ቀስቃሽና ጐትጓች በራሱ ተነሳሽነት የሚያከብር፣ የሚያስከብር ትውልድ ለዚህች ሀገር ያስፈልጋታል፡፡አፍራሽ ተልዕኮ ይዞ የሚንቀሳቀስን የትኛውም ኃይል የሚመክትና ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን የሚጠበቅ ትውልድ ማዘጋጀት ለመፃኢው ህዳሴያችን ዋስትና ሊሆን የሚችል ፤ ዋጋው በምንም ሊተመን የማይችል ትልቅ ስራ ነው፡፡

ምክኒያቱም ያለማናትን፣ ሠላሟ እንዲረጋገጥ ብዙ ዋጋ የተከፈለላትንና ህዳሴዋን ለማረጋገጥ ደፋ ቀና የምንልላትን መተኪያ የሌላትን ሀገር የምናስረክበው ለሀገሩም ለወገኑም ታማኝ ለሆነ ትውልድ ሊሆን ይገባል፡፡ ፆታ እድሜ ቀለም፣ ሀይማኖት ፣ እምነት. . . ወዘተ ሳይለየን በፍቅርና በይቅርታ በመደመር የአንድ ዓላማና አንድ ራዕይ የጋራ ፈፃሚ መሆናችንን በውል የተገነዘበ ትውልድ ለመፍጠር የሚከፈለውን ሁሉ ዋጋ ከፍለን ፤ አቅማችንን አሟጠን ልንረባረብ ይገባል፡፡

 

 የመንግስት ኮዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

ድሬደዋ

                      22/12/2010ዓም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here