ዲያስፖራ ጉዳዮች ማስተባበሪያ አብይ የስራ ሂደት

በኢትዮጵያ የዲያስፖራ ፖሊሲ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው ዲያስፖራ ማለት ከትውልድ አገሩ ከድንበር ባሻገር ርቆ በሌሎች ሉአላዊ አገራት የሚኖር ህዝብ ማለት ነው፡፡

ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ ስንል ከትውልድ ሃገሩ ርቆ በሌሎች አገራት የሚኖር ማለታችን ነው፡፡ አሁን ባለንበት ሁኔታ እንደሚታወቀው ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ምክንያት ከሃገራቸው ወጥተው በልዩ ልዩ ሙያና ስራ ተሰማርተው ይገኛሉ ፡፡ እነዚህ ወገኖቻችን በያሉበት ቦታ የዕውቀት ፤የገንዘብ እንዲሁም የልምድ አቅም ያላቸውና በቴክኖሎጂ የዳበረ ዕውቀት ያላቸው በመሆኑም ለአገር ዕድገት የሚኖራቸው አስተዋጽኦ የላቀ ነው፡፡

ለዚህም ነው መንግሥት ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራ በሀገራቸው ልማት ላይ የሚያደርጉትን ተሳትፎ በክፍተኛ ሁኔታ ለማገዝ የዲያስፖራ ፖሊሲ አውጥቶ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል ፡፡

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውን በአገራቸው እየተካሄደ ባለው የልማትና የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ማሳተፍ በሃገራችን እየተመዘገበ ላለው ፈጣን ዕድገት አጋዥ መሆኑ እሙን ነው አገራችን ወደ ላቀ ልማት ደረጃ ለመሸጋጋር የሚያስችል የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተነድፎ ተግባራዊ ማድረግ በስኬት በማጠናቀቅ የሁለተኛውን የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማዘጋጀት ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ አንገኛለን ፡፡

እስካሁን ባለው ዕቅድ አፈጻጸም አበረታች ውጤት እየተመዘገበ የሚገኝ ሲሆን ፤ በቀጣይም የተጀመረው ዕድገት በማስቀጠል ፍትሃዊና ቀጣይነት ባለው መልኩ እንዲቀጥል ለማድረግና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው የሚኖራቸው የሁለገብ ተሳትፎ ለማሳደግና ራሳቸውንና ትውልድ አገራቸውን መጠቀም እንዲችሉ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት አንደ አገር የዲያስፖራ ፖሊሲ አውጥተን ተግባራዊ በማድረግ ላይ አንገኛለን ፡፡

በመሆኑም በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵውያን የትውልድ ኢትዮጵያውን የአገራቸውን ዕድገት የሁላችንም ፍላጎትና ህልም መሆኑ የማያጠራጥር እንደመሆኑ ከድህነት ከኋላቀርነት ህዝባችንን ለማላቀቅ የሚደረገውን ተስፋ ሰጪና አበረታች የልማት ውጤቶቻችንን ቀጣይነት ለማረጋጋጥ በኢንቨሰትመንት ፤በንግድና ቱሪዝም ፤በዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ፤ ረሚታንስ በአገር ገጽታ ግንባታና በሌሎችም የልማት መስኮች በማበርከት ላይ ይገኛሉ ፡፡

ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች በዓለም ዙሪያ ያላችሁ በዕውቀታችሁ በገንዘባችሁና በሥራ ልምዳችሁ በአገር ልማት ላይ የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደምትችሉ ይታመናል፡፡

 ስለሆነም ወደ አገራችሁ በመግባት አገራችሁን ለመለወጥ የጋራ ጥረት እናድርግ ፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር