የፍትህ፣ ፀጥታና የህግ ጉዳዮች ቢሮ

ሀገራችን የጀመረችውን ቀጣይነት ያለው ልማት ለማምጣት እንዲሁም ዴሞክራሲንና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የረጅምና የመካከለኛ ጊዜ የልማት እቅድ አዘጋጅቶ ተግባራዊ በማድረግ ላይ የምንገኝ ሲሆን፤ ይህንኑ መነሻ በማድረግ በቀጣይ ለአምስት ዓመታት የሚከናወኑ ተግባራት ተለይተው ሀገራዊ በሆነ መልኩ የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ተነድፎ በእንቅስቃሴ ላይ እንገኛለን፡፡

እነዚህን የልማት እቅዶች ማስፈፀሚያ መንገዶች መካከል ከሆኑት አንዱ የሴክተሩን ስትራቴጂያዊ እቅድ አውጥቶ ማስፈፀም ሲሆን፤ ልማቱን በቀጣይነት ለማፋጠን የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መልካም አስተዳደር እና የሕግ የበላይነትን በማስፈን የዜጎችን መብቶችና ነፃነት በማስከበር ላይ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ ይገኛል፡፡

ቢሮው ዘንድሮ የያዛቸውን አቅዶች ለማስፈፀም ከፍተኛ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ሲሆን ፤ ሰፊውን የሕዝብ ንቅናቄ በመፍጠር እስካሁን ያለውን አቅም አሟጠን በተቀላጠፈና ውጤታማ በሆነ አግባብ በመጠቀም ከአጋር አካላት ጋር ከምንግዜውም በተሻለ ቅንጅትና ትብብር ለመስራት ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡