የፍትህ፣ ፀጥታና የህግ ጉዳዮች ቢሮ ራዕይና ተልዕኮ

ራዕይ

የድሬዳዋ አስተዳደር በ2017ዓ.ም የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት፣ ሰላም የሰፈነባት እንዲሁም የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የተከበሩባት ሆና ማየት፤

ተልዕኮ

በድሬዳዋ አስተዳደር የቅመድ ግጭት መከላከል ስራን በመስራት፣ ሰላምና ፀጥታን በማስፈን፣ የህዝብና የመንግስትን መብትና ጥቅም በማስከበር፣ የህግ ጥናት በማድረግ እና ንቃተ ህግ በመፍጠር የህግ የበላይነት ማረጋገጥ፣

እሴቶች

ቢሮው ከህዝብና ከመንግስት የተጣለበትን አደራና ተልዕኮ ለማሳካት በሚያደርገው ጥረት ፍትሀዊ ያልሆነና ኋላ ቀር አሰራሮችን በማስወገድ ሰራተኛውን፣ ስራውንና አገልግሎት ተቀባዩን ማዕከል ያደረገ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕሴቶች ይኖሩታል፡፡

      የስኬታችን መሠረቱ የሰው ኃይላችን ነው፤

      ብቃትና ጥራት ያለው ቀልጣፋ አገልግሎት እንሰጣለን፤

      ከራስ ጥቅም ይልቅ የህዝብ ጥቅም እናስቀድማለን፤

      በህግ የበላይነት እናምናለን፤