የጤና ጥበቃ ቢሮ

ለአንድ አገር ዕድገትና ልማት እንዲሁም ለዜጎች ሁለተናዊ መሻሻል ትምህርት ወሳኝ መሳሪያ ነዉ፡፡ለዚህም አገራችን የመንግስት ስራተኛዉን መብትና ጥቅማ ጥቅም ለማስከበር የተለያዩ መንገዶችን ቀይሳ በመተግባር ላይ ትገኛለች፡፡ ሰራተኛዉም ቁርጠኝነትና ተጠያቂነት ያለዉ ተግባር በመፈፀም እራሱን ብሎም ሀገሩን ወደ ተሻለ ኑሮ ደረጃ መምራት የሚያስችል የዉጤት ተኮር ሚዛናዊ ሥርአት(BSC)ን በመተግበር አስፈላጊ ሆኗል፡፡

ስለሆነም የቀበሌ 05 ትምህርት ማስተባበሪያ ከ2006 በጀት ዓመት ጀምሮ ወደ ትግበራ ለመግባት አዳዲስ የስራ ሂደት ቀረፃን አካቶ የመማር ማስተማር ስራ በትምህርት ግብአት ሂደት የጥራት ችግሮችን ለመሙላት የመምህራንና የርዕሰ መምህራን መብትና ጥቅማ ጥቅም ለማስከበር የሚያስችል ቀልጣፋና ዉጤታማ አሰራርን በመዘርጋት የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ እንዲቻል ማስተባበሪያዉ ዕቅድ አዉጥቶ ይንቀሳቀሳል፡፡