የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ

የተቋምን የአፈፀፃም አቅም በአስፈላጊው ቁሳዊ አደረጃጀት ማደረጃት፣ በውስጡ ያሉትን ሰራተኞች አፈጻጸም በመገንባትና ከወቅቱ የተቋሙ የማስፈጸሚያ ቴክኖሎጆ መሻሻል እና ከአለም አቀፍ የዕድገት አስታንዳርድ እኩል ማሳደግ፣ በተመጣጠነ ወጪ እና ደንበኛን መሰረት ያደረገ ምርት ማምረት ወይንም አገልግሎት መስጠት መቻል የአንድን ተቋም ውጤታማነትና ዘላቂነት በዋናነትያረጋግጣሉ፡፡

በመሆኑም የድሬ ዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ቀደም ሲል የነበረውን ኃላ ቀርና የተንዛዛ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን ከሥር መሠረቱ በማስተካከል ለደንበኞቹ/ለተገልጋዮቹ ቀልጣፋና ጥራት ያለው አገልግሎቶችን ለመስጠትና  ፍላጎታቸውን በይበልጥ ለማርካት እንዲያስችለው የተለያዩ የለውጥ ሥራዎችን በመቀበል ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በአሁኑ ወቅትም በተቋሙየሚስተዋለውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር በአግባቡ በመቅረፍ የሚሰጠውን አገልግሎቶች ደረጃውን የጠበቀና የተገልጋዩን ፍላጎት መሰረት ያደረገ እንዲሆን ለማስቻል ጥረቱን ቀጥሏል፡፡

በዚህም መሠረት ቢሮው ተልዕኮውን በአግባቡ ለማሳካት የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች በማጠናከርና የተጀመሩ የለውጥ እንቅስቃዎችን በይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲያስችለው ይህንን የአገልግሎት አሰጣጥ ቻርተር አዘጋጅቷል፡፡ በመሆኑም ይህ ቻርተር የተቋሙን ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶች፣ በተቋሙ የሚሰጡ የአገልግሎቶች ዓይነትና ደረጃዎች፣ አገልግሎቱን ለማግኘት የሚጠየቁ ቅድመ ሁኔታዎች፣ የተገልጋዮች መብቶችና ግዴታዎች እንዲሁም የቅሬታ አቀባበልና አፈታት ሥርዓትን አካቶ የያዘ ነው፡፡