የውጭ ሃብት ግኝትና አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት

የስራ ሂደቱ ስያሜ፡-    የውጭ ሀብት ግኝትና አስተዳደር ዋና የስራ ሒደት ተብሎ ይጠራል፣

የስራ ሂደቱ ብያኔ

የውጭ ሀብት ግኝትና አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት የመንግስትን የልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እንዲሁም መስተዳደሩ ያለበትን ከፍተኛ የበጀት ጉድለት ለሟሟላት የሚቀርብን ጥያቄ በግብዓት በመጠቀም  የዳሰሳ ጥናት በማካሄድና በጥናቱ ውጤት መሰረት ፕሮጀክት ፕሮፖዛል በመቅረጽ፣ የአሰራር ማኑዋሎችን በማዘጋጀትና ማንዋሎች ላይ ስልጠና በመስጠት፣ የዶነርስ ፎረም በማዘጋጀት ከውጪ በብድርና በእርዳታ እንዲሁም ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሚገኙ ሐብቶችን ወደ አስተዳደሩ እንዲመጡና የበጀት ጉድለቱ እንዲሟላ የሚያደርግ፣ የተገኙትም በመንግስት በጀት ተደራሽ ያልሆኑ ህብረተሰቡ የሚሻቸው የልማት ስራዎች በበቂ ሁኔታ በውጪ ሐብት ፋይናንስ የሚደረግ የሥራ ሂደት ነው፡፡

የሥራ ሂደቱ ራዕይ

በበጎ አድራጎት ማህበራትና ለጋሾች ጋር አጋርነትን በማጠናከር በመንግስት በጀት ተደራሽ ያልሆኑ የልማት ሥራዎች ተሟልቶ ማየት፡፡

ተልዕኮ

አስተዳደሩ ያለበትን የበጀት ክፍተት በማጥናት ልዩ ልዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ፣ የሚቀርቡ ፕሮጀክቶችን በመገምገምና ስምምነቶችን በመፈራረም፣ የዶነርና ኮንፈረንስ በማካሄድ ከውጭ የብድርና እርዳታ እንዲሁም ከበጎአድራጎት ድርጅቶች የሚገኙ ሀብቶችን ወደ አስተዳደሩ በመከታተል አስተዳደሩ ያለበትን የልማት ክፍተት ማሟላት፡፡

የሥራ ሂደቱ ዋና ዋና ተግባራት

 1. የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ማካሔድ
 2. ፕሮጀክት መቅረጽና የመጡ ፕሮጀክቶችን መገምገም
 3. ዕቅድ ማሰባሰብና ማጠናከር፤
 4. ከመልቲ-ላተራል ድርጅቶች በጀት በማሰባሰብ ድልድል ዝግጅት በማድረግ በጀቱን ማስተዳደር
 5. ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ምዝገባ፣ እድሳትና የተለያዩ ድጋፎችን መስጠት
 6. መልቲ-ላተራል ፣ የበጎ አድራት ማህበራትና የእድሮችን ፕሮግራሞችን/ፕሮጀክቶችን በመስክ መከታተል /Monitoring/ እና ሪፖርት ማቅረብ
 7. መልቲ-ላተራል፣ የበጎ አድራጎት ማህበራትና የእድሮችን ፕሮግራሞች/ፕሮጀክቶችን በመስክ መከታተል/Evaluation/ እና ሪፖርት ማቅረብ
 8. የፕሮጀከት ማጠናቀቂያ ተርሚናል ኢቫለዌሽን ማድረግ፡፡
 9. ከተጠቃሚዎች የእንደገና ዕቅድ /Reprogramming /ጥያቄ ማስተናገድ
 10. ሪቪው ሚቲንግ ማካሄድ
 11. ለበጎ አድራት ድርጅቶችና የለጋሾች ፕሮፋይል ማዘጋጀት
 12. ክፍተትን በመለየት የአቅም ግንባታ ተግባራት ማከናወን
 13. የበጎ አድራጎትና የለጋሽ ድርጅቶችን ፕሮጀክቶችን ፋይዳ ጥናት /Impact Assessment/ ማካሄድ
 14. የአፈፃፀም ሪፖርት ዝግጅት
 15. Channal-3  የሚመጣ ሀብት የክትትልና የምዝገባ ሥራ መስራት
 16. የጽሑፍና ዘገባ ተግባራቶች