የኮንስትራክሽን ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ

በኮንስትራክሽንና ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት ቢሮ ባለፉት አምስት ዓመታት በከተማ ልማት፣ በቤቶችና፣ በኮንስትራክሽን ዘርፍ እንደሌሎቹ ዘርፎች ሁሉ ፈጣን ልማትን በማረጋገጥና ለመልካም አስተዳደር ግንባታ መሰረት በመጣል በአስተዳደራችን የተጀመረውን የትራንስፎርሜሽን እንቅስቃሴ በተሳካ አኳኋን እንዲቀጥል የሚያስችሉ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪውን የኋላ ትስስር በማጠናከር ለሲሚንቶ፣ ለኤሌክትሪክና ለሳኒተሪ ዕቃዎች፣ ለማሽነሪ፣ ለብረታ ብረትና ቆርቆሮ ምርቶች ገበያ በማመቻቸት ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ ነው፡፡ የፊት ትስስር በማጠናከር በሪል እስቴት እና የሌሎች አገልግሎቶች መስፋፋትም ላይ አዎንታዊ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው፡፡

በአስተዳደራችን ያለውን የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ በተቀናጀና አግባብነት ባለው መልኩ ከማስኬድ አንጻር በህንጻ ህጉ ኢንዲመሩ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን በኮንስትራክሽን ኢንዲስትሪው የሚሰማሩ ባለሞያዎችን ከመመዝገብ በተጨማሪ ብቁ ሆነው በኢንደስትሪው እንዲሰማሩ የመመዘን ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

በማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶችም ሰፊ የማሻሻያ ተግባራት ተካሂደዋል፡፡ የአሰራር ሂደቱ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ከማካሄድ አንስቶ አገልግሎቶችን ባልተማከለ ደረጃ የመስጠትና በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንቅስቃሴ ማካሄድ ተችሏል፡፡

በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመንም በከተማችን የሚታየውን የልማት የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ለመቅረፍ ቢሮው ከሀገራዊው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የድርሻውን በመውሰድ ለከተማዋ ሁለንተናዊ እድገት የበኩሉን ለማከናወን በጥሩ ቁመና ላይ ይገኛል፡፡ በእቅድ ዘመኑ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በማስፋፋት በከተማዋ የሚታየውን የስራ አጥነት ችግር ለማቃለል አልፎም በነዋሪዎች መካከል ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እንዲሰፍን በማስቻል በኩል አበረታች ውጤት ለማስመዝገብም ከመቼውም በላይ በትጋት ይሰራል፡፡