ምክር ቤት የቢሮው ሀላፊ መልእክት

አቶ  ከድር ጁሃር – የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ

 

የአፈ ጉባኤ መልዕከት

ምክር ቤታችን በድሬዳዋ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 መሰረት ከአስተዳደሩ ህዝብ የተወከለ እና ሉዓላዊ ስልጣን በውክልና የተሰጠው ከፍተኛ ሥልጣን ያለው ህገ መንግስታዊ ተቋም ነው፡፡  

ምክር ቤታችን ከተማና ገጠሩን የወከሉ 119 ወንድ 70 ሴት አባላት ያሉት ሲሆን ፤ የተጣለበትን ተግባርና ኃላፊነት በሚገባ ለመወጣት በተሻሻለው የምክር ቤቱ የአሠራርና የአባላት ሥነ ምግባር ደንብ ቁጥር 11/2009 መሠረት በየጊዜው ራሱን እየፈተሸ   የሀገሪቱን ፖሊሲዎች ስትራቴጂዎችና ፕሮግራሞች  እንደ አስተዳደሩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ  ተጨባጭ ሁኔታ እንዲፈፀሙ ማስቻል ፤ ለአስተዳደሩ ጉልህ አስተዋጽኦ ያላቸው ህጎች ማውጣትና ተፈጻሚነታቸው መከታተልና መቆጣጠር ፤ በመንግስት አካላት መካከል ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት ፤ በመልካም አስተዳደር የነዋሪውን ተጠቃሚነት ማረጋጥ የመሳሉት ዋና ዋና  ተግባራቱ ናቸው፡፡

ምክር ቤታችን የህዝብ ውክልናን ከመወጣት ኃላፊነቶቹ ጎን ለጎን ባካሄዳቸው የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች እና በሰጣቸው ግብረመልሶች የአስፈጻሚውን ውጤታማነት ለማጎልበት ከማስቻሉም በላይ የህዝብና የመንግስት ሀብትና ንብረት ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ የአሠራር ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲዳብር የሚደረጉ የክትትልና ቁጥጥር ሥራዎች በቀጣይ ይበልጥ በማጠናከር ውጤታማ ለማድረግ ከምንግዜውም በላይ እንድንረባረብ ከህዝብ የተጣለብንን አደራ ለተጠቃሚዎች ፣ ለባለድርሻ አካላት መረጃ ለመስጠትና ለተቋሙ እርካታ የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ለማስቻል ይህ ፖርታል መዘጋጀቱን ሳበስር በደስታ ነው ፡፡

አመሰግናለሁ!!