የሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሮክቶሬት መልዕክት 

የዳይሮክቶሬቱ  መልዕክት 

በሃገራዊ የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ አቅጣጫችን ላይ በግልፅ እንደተመለከተው በህዳሴ ጉዟችን የመጀመሪያው ምዕራፍ የምናሳካው ዋናው ጉዳይ ለልማት ፕሮግራሞቻችን ማስፈፀሚያ አስፈላጊ የሆኑ ውጤታማ የውጭ ቴክኖሎጂዎችን የመለየት፤ የመምረጥ፤ የማስገባት፤ የመጠቀም እና የማላመድ አቅምን ማሳደግ ነው፡፡ ይህ ምዕራፍ ለቀጣይ የህዳሴ ጉዟችን ምዕራፎች መሰረት የሚጣልበትና ከአንዱ ምዕራፍ ወደ ሌላው ምዕራፍ የሚደረገውን ሽግግር ያላመንገራገጭ ለመፈፀም መደላደል የሚፈጠርበት፤ እጅግ ፈታኝና ከፍተኛ ጥረት የሚጠይቅ፤ ወሳኝ ምዕራፍ ነው፡፡ በመሆኑም የእያንዳንዱን የዘርፉ ተዋናዮችና ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ጥረትና ርብርብ የሚጠይቅ ነው፡፡

ሀገራችን በሚፈለገው ደረጃ ላለማደጓ  ዋናው ምክንያት ቴክኖሎጂ የማመንጨትና የመጠቀም አቅሟ አነስተኛ በመሆኑ ቢሆንም አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ቶሎ ለማደግ የግድ አዲስ ቴክኖሎጂ ማፍለቅ አያስፈልጋትም፡፡ ይልቁንም ሌሎች ያፈለቁትን ቴክኖሎጂ ቶሎ ቶሎ መጠቀም በመቻል በ2017 መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ደረጃ መድረስ ነው፡፡ ይህ ማለት ያደጉ ሀገራት በሄዱበት የቴክኖሎጂ እድገት ደረጃ በተመሳሳይ መልኩ መድገም ሳይሆን ዘግይቶ የመጣ እድልን በመጠቀም በዓለም ላይ ያሉትን የምርምር ውጤት የሆኑትን ጠቃሚ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት፣ ቴክኖሎጂን የመረዳት፣ የመጠቀምና ከነባራዊ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ የማሻሻል አቅም እንዲፈጠር ማድረግ ይጠበቃል፡፡

ይህንን እውን ለማድረግ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ ያለውን የቴክኖሎጂ መስፋፋትና የኢኖቬሽን ስራዎችን ለማበረታታትና ለመደገፍ አስፈላጊ የሆኑ ውጤታማ ቴከኖሎጂዎችን ለማፈላለግ፣ ለመምረጥ፣ ለማስገባት ለማላመድና ለመጠቀም የሚደረጉ ጥረቶችን ያግዝ ዘንድ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አደረጃጀት ወደ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እንዲወርድ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

በመሆኑም አስተዳደራችን አገራዊ አቅጣጫን በመከተል በአስተዳደሩ ያለውን የኢንዱስትሪ  ኮሪደርነት ሚና በበቂ ሁኔታ ለመደገፍ የሚያስችል አደረጃጀት መፍጠር በማስፈለጉ በአስተዳደር ደረጃ ተጠሪነቱ ለከንቲባው እና ለካቢኔ ጉዳዮች ጽ/ቤት የሆነ የሳይንስና ቴክኖሎጂ አደረጃጃቱን መሰረት በማድረግ የሰው ሀይሉን በማሟላት ወደ ሙሉ ትግባር የገባ ሲሆን ዳይሮክቶሬቱ አዲስ ከመሆኑ አንፃር የመላ የአስተዳደራች ህዝቦች ፣መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማቶች ለዳይሮክቶሬቱ ዓላማ ስኬት ሁሉም የበኩሉን አስተዋፆ እንዲያደረግ በአክብሮት መልክቴን አስተላልፋለው፡፡