የሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሮክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት

ሳይንስና፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቪሽን ስንል?

ሳይንስና ስንል ነባራዊውን አለም እና የተፈጥሮ ህግጋትና ክስቶችን ለማብራራትና ለመገንዘብ የሚያስችለንን እውቀት በምልክታና በሙከራ የምናገኝብት ዘዴ ነው፡፡ አለማችን ወደ አንድ መንደርንት መምጣትዋን የተለያዩ ውጤቶችን ያሳየናል፡፡ ከነዚህም አንዱ በአለም ውስጥ የሚከናወኑትን ተግባራትን  በደቂቃዎች ውስጥ ሰዎች የሚያውቁትን የመረጃ መስመር መዘርጋቱ ነው፡፡ ለዚህም ሳይንስ ወለድ የሆኑት የቴክኖሎጂ ውጤቶች ተጠቃሽ ናቸው፡፡  ቴክኖሎጂ ማለት የአንድን ህብረተሰብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታትና የኑሮ ደረጃውን ለማሻሻል የሚያስችል፣ የሸቀጦችና አገልግሎቶች አመራርነት ከአጠቃቀም ጋር የተጣመረ ዕውቀት የድርጊት ጥበብ የአሰራር ዘዴና ስርዓት ነው፡፡

ኢኖቪሽን ማለት ደግሞ የተፈጠረ ቴክኖሎጂን የሚያሻሻል፣ ለነበረ ቴክኖሎጂ አዲስ የጥሬ እቃ ምንጭ ወይም አዲስ ገበያ የማስገኘት ወይም በነበረ ቴክኖሊጂ ላይ በሚል ቴክኖሎጂውን የተሸሻለ፣ የቀለጠፈ ወይም በዚህ የማሻሻል ስራ የተነሳ የማምረቻ ወይም የአገልግሎት ጊዜንና ወጪን የሚቀንስ ወይም ገበያን የሚያስፋ ቴክኒካዊ የመፍተሔ ሀሳብ ነው፡፡

በድሬደዋ አስተዳደር በከንቲባ ጽ/ቤት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት ዳሮክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት

ዳይሬክቶሬቱ ተጠሪነቱ ለከንቲባው ሆኖ የሚከተለው ተግባርና ኃላፊነት ይኖረዋል፡፡

 1. የአስተዳደሩን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እድገት ዓላማዎችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎችን መደገፍ
 2. በአስተደደር ደረጃ ያለ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እውቀቶችን ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማስቻል፡፡
 3. በአስተዳደር ደረጃ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢኖቬሽን ስርዓቱ ውጤታማ እንዲሆን የመደገፍ ስራ ማከናወን
 4. የኢንዱስትሪውን እድገት ሊያሳልጡ የሚችሉ የምርምር የቴክኖሎጂ ሽግግርና ልማት ስራዎችን መደገፍ
 5. በኢኖቬሽን ስራዎች ላይ የሚካሄዱ አመታዊ የሲምፖዚየም ዝግጅቶች ላይ የሚሳተፉ ኢኖቬተሮችን ማስተባበር
 6. የቴክኖሎጂ ፓርኮች እንዲቋቋሙ እና የቴክኖሎጂ እውቀት ለማሳደግ የሚያስችል አሰራር ስርዓቶች የሚተገበሩበትን መንገድ ማመቻቸት መደገፍና መከታተል
 7. የሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበቦች በትምህርት ቤቶች እንዲቋቋሙ እንዲሁም በህብረተሰቡ ውስጥ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ውጤቶች እንዲተዋወቁ ማድረግ
 8. በሳይንስና ቴክኖሎጂ ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡና የፈጠራ ክህሎት ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተቋማትን  መደገፍና ማበረታታት
 9. የጨረራ አመንጪ መሳሪያዎችን በመለየትና በመከታተል የአስተዳደሩን ህብረተሰብ ከሚከሰቱ ጉዳቶችን የመከላከል፣
 10. በአስተዳደሩ የሚሰጡ ምርቶችና አገልግሎቶችን የጥራት ደረጃቸው የተሟላ መሆኑን ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር ክትትል በማድረግ አፈፃፀሙን መከታተል
 11. በአስተዳደሩ የሚገኙ የኢንዱስትሪና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በዘመናዊ አለካክ ዘዴ የፍተሻና የእንስፔክሽን አገልግሎት እንዲያገኙ ማስተባበር
 12. በአስተዳደሩ የሚገኙ ፈጠራዎችን የአይምሯዊ ንብረት መብት ጥሰቶችን መከላከል፣የንብረት መብት ጥበቃና ልማት ጥበቃና ግንዛቤ ስራ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ማከናወን
 13. በሂደቱ የሚከናወኑ ተግባራትን የእቅድ ዝግጅት ማስተባር መደገፍ መከታተል ስራና ማከናወን
 14. ሌሎች ለስራ ሂደቱ የተሰጡ ተልዕኮዎችን ለማሳካት የሚያስችል ተግባራትን ያከናውናል፡፡

አድራሻ:

በድሬደዋ አስተዳደር  በከንቲባ  ጽ/ቤት  የሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት ዳይሮክቶሬት

ስልክ – 0251119576