የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ተልዕኮና ራዕይ

 1. የቢሮው ተልዕኮ

     ተልዕኮችን «አስተማማኝ የመንግስት መረጃ ልውውጥን በማስፈን ፣ በሙያ ክህሎቱ የዳበረና በከፍተኛ ስነ-ምግባር የታነፀ የኮሙዩኒኬሽን ልማት ሠራዊት በማፍራት ፣ ስትራቴጂያዊ አመራር በመስጠት መረጃን መሰረት ያደረገ ተሳታፊ ህዝብ ፣ የጋራ መግባባት የሰፈነበት ፣ በጎ ገፅታ ጎልቶ የወጣበትና የፈጣን ምላሽ አሰራር ያዳበረ አስተዳደር እውን ማድረግ ነው፡፡

 1. የቢሮው ራዕይ

<< በ2012 በጠንካራ የኮሙዩኒኬሽን ልማት ሠራዊት የታገዘ አስተማማኝ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ተፈጥሮ ማየት፡፡ >>

 1. የቢሮው እሴት
 • በዕውቀትና በሙያ ብቁ ሆኖ መገኘት፣
 • የመረጃ ኃይል ሆኖ መገኘት፣
 • ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ፣
 • ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነትን አምርሮ መታገል፣
 • ለዕድገትና ብልፅግና መስራት፣
 • ለሥርዓተ ፆታ ስኬታማነት በጽናት መስራት፣

የቢሮው ስልጣንና ተግባር 

ቢሮው የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡

 • የአስተዳደሩ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ስራን በበላይነት ይመራል፣ያስተባብራል፤
 • የአስተዳደሩ የኢንፎርሜሽን ዋነኛ ምንጭ በመሆን ያገለግላል፤ በልዩ ልዩ መንገዶች ያሰራጫል፤ በዋና ዋና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ የመንግስትን አቋም ይገልፃል፤
 • የአስተዳደሩን ሴክተር መስሪያ ቤቶችን የሕዝብ ግንኙነት ስራ አቅጣጫን ያስቀምጣል፤ ያስተባብራል፤
 • ብሄራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችሉና የአስተዳደሩን መልካም ገፅታ የሚያጎለብቱ ሁነቶችን ይፈጥራል፤ ያስተባብራል፤ ያስተዋውቃል፤ በነዚህ ተግባራት ላይ የሚያተኩሩ የሚዲያ ፕሮግራሞች እንዲዘጋጁና እንዲሰራጩ ያደርጋል፤
 • በአስተዳደሩ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን እንዲሁም በብሄራዊ መግባባት እና በገፅታ ግንባታ ስራዎች ከሴክተሮች፣ ከቀበሌዎች፣ ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር የግንኙነት ስርዓት ይዘረጋል፤ ተፈፃሚነቱን ይከታተላል፤
 • የአስተዳደሩ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና ወረዳዎች የሕዝብ ግንኙነት ሠራተኞችን የአቅም ግንባታ ተግባሮችን ያከናውናል፤ የሰራተኞቹንም ምልመላና ቅጥር በተመለከተ አስፈላጊውን ድጋፍ ይሰጣል፤
 • የሚዲያ ሞኒተርኒግ፣ የፕሬስ ዘገባ፣ የከባቢያዊ ቅኝት ስራዎችን ያከናውናል፤ ትንተና ያዘጋጃል እንዲሁም የህዝብ አስተያየት ያሰባስባል፤
 • ሚዲያዎች ከአስተዳደሩ ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት ያስተባብራል፤ ለሚዲያ ኢንፎርሜሽን ጥያቄ አግባብ ባላቸው የመንግስት አካላት ምላሽ እንዲሰጥ ያደርጋል፤ ዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ክንውኖችና ሁነቶች ተገቢው የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጣቸው ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
 • በመንግስት ፖሊሲዎችና በተለያዩ አስተዳደራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ግንዛቤ ለመስጠትና ግልፅነትን ለመፍጠር ሕዝባዊ የውይይት መድረኮችን ያዘጋጃል ያስተባብራል፤
 • ከፍተኛ የአስተዳደሩ ባለስልጣናት ህብረተሰቡን በአካል አግኝተው እንዲያነጋግሩና ተቋማትን ፣ድርጅቶችን ፣ሁነቶችን፣የስራ አፈፃፀሞችንና ክንውኖችን እንዲጎበኙ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
 • ልዩ ልዩ የሕትመትና የኦዲዮቪዲዮ ምርቶችን ያመርታል፤ የአስተዳደሩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የፎቶ ግራፍና የኦዲዮቪዲዮ ቀረፃ፣የአርማና የህትመት ዲዛይን እንዲሰራላቸው ሲጠይቁ የማዘጋጀትና የማማከር አገልግሎት ይሰጣል፤
 • ለንግድ አላማ የሚታተምም ሆነ የንግድ ዓላማ ለሌላቸው ስርጭታቸው በአስተዳደሩ ብቻ ለሆኑ ጋዜጦችና መጽሔቶች የሙያ ፍቃድ ይሰጣል፤  በሕጉ መሰረት መሰራታቸውን ይከታተላል፤
 • የማስታወቂያ የስራ ህግን ተከትሎ ለአስተዳደሩ እና ለሀገር ልማት አስተዋፅኦ ሊያደርግ በሚችልበት አቅጣጫ ስለመከናወኑ ክትትልና ቁጥጥር ያደርጋል፤
 • በአስተዳደሩ ውስጥ በቋሚ የዜና ወኪልነት ለሚመደቡ የውጭ አገር እና የአገር ውስጥ የዜና ወኪሎች ፍቃድ መውሰዳቸውን ያረጋግጣል፤ ህግ አክብረው መስራታቸውን ይከታተላል፤
 • የመንግስት ፖሊሲዎችን ለማስተዋወቅና ለገጽታ ግንባታ የሚረዱ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራም ያዘጋጃል የአስተዳደሩ መስሪያ ቤቶች እንዲሰራላቸው ሲጠይቁ ያዘጋጃል ያማክራል፤
 • በአስተዳደሩ ለሚገኙ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገራት ጋዜጠኞች እንደ አስፈላጊነቱ መግለጫዎችን ይሰጣል፤
 • አስተዳደሩ ሊታወቅበት በሚገባው ትክክለኛ ገጽታ እንዲታወቅ ሰፊ መረጃ ይሰጣል፣በአስተዳደሩ ላይ የሚሰነዘሩ የተሳሳቱ መረጃዎች ላይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
 • በኮሙዩኒኬሽን ስራ ዙሪያ በሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ ወገኖች መካከል በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ የአጋርነት ስርዓት ይዘረጋል፤
 • ዓላማውን ለማሳካት የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡