የህግ ማርቀቅ፣ ንቃተ ህግና የምክር አገልግሎት መስጠት አብይ የስራ ሂደት

  • በጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተ ምክርና አስተያየት ለአስተዳደሩ የመንግስት አካላት በመስጠት የመንግስት ፖሊሲዎች ውሳኔዎች የሀገሪቱ ህገ-መንግስት ፣ የአስተዳደሩን ቻርተር፣ አለም አቀፍ ስምምነቶችንና ሌሎች ህጎችን የተከተሉ እንዲሆኑ እገዛ ያደርጋል፡፡
  • ለአስተዳደሩ ምክር ቤትና ካቢኔ የሚቀርቡ ማናቸውም የህግ ማርቀቅ ስራ በበላይነት ይመራል እንዲሁም የህግ አስተያየት በመስጠት ድጋፍ ያደርጋል፡፡
  • በአስተዳደሩ የህግ ጥናትና ምርምር ያደርጋል፡፡ በውጤቱም መሰረት ማሻሻያዎች እንዲያደርጉ አስተያየት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፡፡
  • የአስተዳደሩን ነዋሪዎች ንቃተ ህግ ለማዳበር በተለያየ ዘዴዎች የህግ ትምህርትና ስልጠና ይሰጣል፡፡
  • ስለ ጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥ ደንብና መመሪያ አዘጋጅቶ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፡፡