ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ

የመ/ቤቱ ስልጣን ኃላፊነትና ዋና ዋና ተግባራት

የንግድ ኢንዱሰትሪና ኢንቨስትመንት  ቢሮ የድሬዳዋ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላትን እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር —– 2002 ዓ.ም ተጠሪነታቸው ለከንቲባ ሆነው ከተቋቋሙ ቢሮዎች መካከል አንዱ ሲሆን የባህልና ቱሪዝም ኤጀንሲ፣ልማታዊ ባለሃብት የመሳብና የማብቃት አብይ የስራ ሂደት፣ፍትሃዊ የንግድ አሰራርና ልማት አብይ የስራ ሂደት፣የህብረት ስራ ማደራጀትና ልማት አብይ የሥራ ሂደት እንዲሁም የኢንደስትሪ ልማት ዓብይ የስራ ሂደትን በበላይነት የሚያስተባብርና የሚመራ ሲሆን የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡፡

የቢሮው የስልጣን ኃላፊነትና ዋና ዋና ተግባራት

 1. በአስተዳደሩ በንግድ ስራ ለሚሰማሩ የሀገር ውስጥ ዜጎች የንግድ ስራ ፈቃድ ምዝገባ ያደርጋል ፈቃድ ይሰጣል ያድሳል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በህጉ መሠረት ይሰርዛል፡፡
 2. የንግድ ማህበራትን የመተዳደሪያ ደንብና የመመስረቻ ጽሁፍ የማሻሻልና የስረዛ ቃለ ጉባኤዎችን እንዲሁም በአዲስ የሚቀርቡትን ያጸድቃል ፈቃድ ይሰጣል፣ያድሳል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም በህግ መሠረት ይሰርዛል፤
 3. በአስተዳደሩ የንግድ እቃዎችና የአገልግሎት ሰርጭት የገበያ ህግና ስርዓትን የተከተለ መሆኑን ያረጋግጣል፤ተገቢ ሆኖ ሲገኝም ገበያው ሊረጋጋ የሚችልበት ሁኔታ ያመቻቻል፤
 4. በአስተዳደሩ የሚገኙ የገበያ ማዕከላትን ደረጃ ያወጣል፣ደረጃቸውን የጠበቁ ማዕከላት መገንባታቸውን ይቆጣጠራል፤ሊያድጉና ሊስፋፋ የሚችሉበትን ሁኔታም ይቀይሳል፤
 5. በአስተዳደሩ የንግድ ቁጥጥርና ክትትል ስራዎችን በማከናወን የህግ ወጥ ንግዱ ስራዎችን ይከታተላል ተገቢ ሆኖ ሲገኝ እርምጃዎችን በመውሰድ የንግድ ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ ያደርጋል፤
 6. የኢንዱስትሪ ልማትን ለማፋጠን የሚያስችል የተመቻቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ስልት ይቀይሳል፤ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፤
 7. በአስተዳደሩ ለኢንዱስትሪና ለኢንቨስትመንት ሊውሉ የሚችሉ መረጃዎችን ያሰባስባል፤ያጠናክራል፤ይተነትናል፤ለተጠቃሚዎች የሚሰራጩበትንና ለልማት ግብዓት ሊውሉ የሚችሉበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
 8. በአስተዳደሩ ንግድ እና ኢንዱስትሪ እንዲስፋፉ የንግድ ትርዒትና ባዛር፣አውደ ራዕዮች እንዲዘጋጁ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤
 9. የአስተዳደሩን የሀብት ክምችት መነሻ በማድረግ የኢንቨስትመንት አማራጮችን የሚያመላክቱ  ጥናቶችን ያካሄዳል፤ባለሃብቶችን ለመሳብ የሚያስችሉ ስልቶችን ይቀይሳል፤
 10. የኢንቨስትመንት ፈቃድ ነክ አገልግሎቶችን ይሰጣል፤ያድሳል፤አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በህግ መሠረት ይሰርዛል፤
 11. ለባለሃብቶች የተፈቀደ የመሬትና ሌሎች የማበረታቻ ድጋፎች ተግባራዊ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትልና ያደርጋል፤
 12. የኢንዱትስሪ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚያስችል ቀልጣፋ የአሰራር ስርዓት ይዘርጋል፡፡ አፈፃፀሙን ይከታተላል ይገመግማል፤
 13. አስተዳደሩ በሃገር ውስጥና ከውጭ ሃገራት ጋር በኢንዱሰትሪ ምርት የገበያ ዕድል ጠንካራና ተወዳዳሪ የሚሆንበትን ስልት ይቀይሳል ተግባራዊነቱን ይከታተላል፤
 14. በአስተዳደሩ የሚገኙ ኢንዲስትሪያሊስቶች ከሌሎች ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
 15. በአስተዳደሩ የሚገኙ ማህበራትን ያደራጃል ምዝገባና ህጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ይሰጣል፤
 16. ለማህበራት የአቅም ግንባታ፣ የግብዓትና ፋይናንስ አገልግሎት ምችችት ይፈጥራል፤
 17. የማህበራትን የኦዲትና የኢንስፔክሽን ሪፖርት ያዘጋጃል ያሰራጫል አፈፃፀሙንም ይከታተላል፤
 18. ለማህበራት የህግና የምክር አገልግሎት ይሰጣል፤
 19. አለማውን ለማሳካት የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፤