ምክር ቤት

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት

 1. መግቢያ

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በድሬዳዋ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 416/1996 መሰረት የተሰጠዉን ሥልጣንና ተግባር እንዲሁም ከህዝቡ የተጣለበትን ኃላፊነት መወጣት እንዲችል በግልጽነት ፣ በተጠያቂነት እና በአሳታፊነት ላይ የተመሠረተ የአደረጃጀት እና የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የተቋቋመ የአስተዳደሩ ሥልጣን መገለጫ ተቋም ነው፡፡ ምክር ቤቱ ሀምሌ 5 ቀን 2000 በህዝብ በተመረጡ 189 የምክር ቤት አባላት የተመሰረተ ሲሆን ፤ የመጀመሪያውን የስራ ዘመንም በማጠናቀቅ ሁለተኛ የስራ ዘመኑን ምክር ቤቱ ከሐምሌ 5 ቀን 2006 ጀምሮ ለምክር ቤቱ የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነት ህግ በማውጣትና  በማጽደቅ እንዲሁም በአስፈጻሚ አካላት የእቅድ ክንውን ላይ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል፡፡

በዚሁ መሰረት ምክር ቤቱ ለመልካም አስተዳደር መስፈን ፣ ለሰብአዊ መብቶች መከበር ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታና ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትን ለማረጋገጥ የሚውሉ እስከ አሁን 61 አዋጆችና 12 ደንቦችን በተጠናከረ የህዝብ ተሳትፎ በማውጣትና ተግባራዊነታቸውን በመከታተልና በመቆጣጠር የአስተዳደሩ ህብረተሰብ በምክር ቤቱ የሚወጡ ህጎች ላይ የዳበረ እውቀት እንዲኖረው በማድረግ በአስፈጻሚው አካላት የታቀዱ እቅዶች አፈጻጸማቸው ተጨባጭ የኑሮ መሻሻል ማስመዝገብ እንዲችሉ በሚደረገው እንቅስቃሴዎች ውስጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ በማድረግ ሃላፊነቱን በመወጣት ላይ የሚገኝ አካል ነው፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በህዝብ የተጣለበትን አደራና ህገ-መንግስታዊ ሃላፊነቱን በመወጣት ለተገልጋይና ለባለድርሻ አካላት ስለተቋሙ ነባርና ወቅታዊ መረጃዎች ለመስጠት ይህ በአስተዳደሩ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሰርቨር ላይ የሚጫን አጭር ፅሁፍ አዘጋጅቷል፡፡

 1. የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ራዕይ ተልዕኮ እና እሴቶች 

ራዕይ

በድሬዳዋ አስተዳደር የዳበረ ዴሞክራሲ ፣ ባህል ፣ መልካም አስተዳደር ፣ ዘላቂና ቀልጣፋ የሆነ ሁለንተናዊ የልማት እድገት እውን ሆኖ ማየት፡፡

ተልዕኮ

ለመልካም አስተዳደር መስፈን ፤ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እንዲሁም ዘላቂ እና ፈጣን ኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ለማረጋገጥ የሚውሉ ህግ፣ አዋጆችና ደንቦች በተጠናከረ የህዝብ ተሳትፎ ማወጣት ፣ ተግባራዊነታቸውን መከታተል እና መቆጣጠር ፣ ውክልናውን በመወጣት የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፡፡

እሴቶች

 • ለህገ- መንግስቱ እና ለመራጩ ህዝብ ተገዥ መሆን፣
 • የአሰራር ስርዓት ግልጽነት ና ቅልጥፍና ታማኝነትና የህዝብ አገልጋይነት ስሜት መፍጠር ፣
 • መቻቻል እና የጋራ መግባባትን ማስፈን ፣
 • የዘር የሃይማኖት የጾታ እና የፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳይደረግ ለሁሉም ፍትሃዊ አገልግሎት መስጠት ፤
 • ግልጽነት ፤ ቅንነት አሳታፊነት እና የተጠያቂነት መንፈስ መፍጠር ፡፡
 1. የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ጽህፈት ቤትየድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤትን ዓላማ አስፈፃሚና የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችንና የምክር ቤቱን አስተዳደራዊ ስራዎች አደራጅቶና አቀናጅቶ ለመምራት በሚያስችል መልኩ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1/2000 የተቋቋመ ጽህፈት ቤት ነው፡፡–  ጽህፈት ቤቱ ተጠሪነቱ ለምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ራዕይ ተልዕኮ  እና እሴቶች

ራዕይ

በ2012 በተሟላ ሙያዊ ድጋፍና አስተዳደራዊ አገልግሎት አሰጣጥ በሀገሪቱ ውስጥ ተምሳሌት የሆነ ምክር ቤታዊ አገልገሎት ሰጭ ጽ/ቤት ሆኖ መገኘት፤

ተልዕኮ

የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት የምክር ቤት አባላትና አካላት የህግ አወጣጥ ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም የውክልና ሥራ በተገቢው መንገድ እንዲከናወኑ ሙያዊ ድጋፍ እና አስተዳደራዊ አገልግሎት በተሟላ መልኩ መስጠት ፡፡

እሴቶች

 • የህግ የበላይነትን አክባሪነት ፣
 • የመልካም ስነ – ምግባሮች ባለቤትነት ፣
 • ለመንግስት ሃብትና ንብረት ተቆርቋሪነት ፣
 • የተገልጋዮችን ክብርና ሞገስ መጠበቅ ፣
 • የጎለበተ የሃላፊነት ስሜት ፣
 • ያለአድሎ መስራት፤ ለለውጥ መስራት ፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ጽ/ቤት አደረጃጀት

 1. አፈ-ጉባኤ
 2. ምክትል አፈ-ጉባኤ
 3. የምክር ቤቱ አባል የሆነ አንድ ፀሀፊ
 4. ብዛታቸው እንደአስፈላጊነቱ በምክር ቤቱ የሚወሰኑና የሚሾሙ የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ በሹመት የሚመደቡ የስራ ኃላፊዎች እና
 5. አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞች አሉት
 6. የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት ሠራተኞች በድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ሠራተኞች አዋጅ መሠረት ይተዳደራሉ
 1. በጽህፈት ቤቱ ስር ያሉ ሂደቶች
 1. አፈ ጉባኤ
 2. ምክት አፈ ጉባኤ
 3. የምክር ቤቱ ፀሐፊ
 4. የህግ አወጣጥ ክትትልና ቁጥጥር ሙያዊና አስተዳደራዊ ድጋፍ አሰጣጥ  ዳሮክቶሬት
 5. ህዝብ ግንኙነት ዳይሮክቶሬት
 6. የስርዓተ ጾታና ኤች አይቪ ጉዳይ
 7. የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሮክቶሬት
 8. የግዥ ይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሮክቶሬት