የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ወገንን የመርዳት ባህል እንድናዳብር አቅም ፈጥሮልናል -ወጣቶች

0
168

በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር በመላ ሀገሪቱ ከ10-ሚሊዮን በላይ ወጣቶች የሚሳተፉ ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር 60ሺ ወጣቶች ይሳተፋሉ፡፡

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ጉልበታቸውን፣ እውቀታቸውንና ሃብታቸውን በማስተባበር ወገንን የመርዳት ባህል እንዲያዳብሩ አቅም የፈጠረላቸው መሆኑን ወጣቶች ገለፁ፡፡

ባለፈው ቅዳሜ በችግኝ ተከላ ስነ ስርዓት የተጀመረው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በያዝነው ክረምት ከ60ሺህ በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት መሰማራታቸውን የአስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ኮምሽን ኮምሽነር እና ኡመር አስታውቀዋል፡፡

 

ኮሙሽነር እና አክለውም በክረምት የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር በ7 አገልግሎት ዘርፎች በመሰረታዊነት ስራዎች ይሰራሉ፡፡ በመርሃ ግብሩም ከ55 ሚሊዮን ብር በላይ የአስተዳደሩን ወጪ ማትረፍ ይቻላል ብለዋል፡፡

ኮምሽነር አና ለተሳታፊ ወጣቶች ባስተላለፉት መልዕክት ድሬዳዋ በዘር፣ በብሔር፣ በጎጠኝነትና፣ በእምነት ተከፋፍለን የምንኖርበት ከተማ ባለመሆኗ ሁላችንም የቀድሞ እሴቷን በማስጠበቅ አብሮ የመኖር ባህሏን የመጠበቅ ኃላፊነት ወጣቱ ትልቁን ድርሻ በመውሰድ ያለንን በማካፈል የፍቅር ከተማ መሆኗን መመስከር መቻል አለብን ብለዋል፡፡

“በጎ ፈቃደኝነት ለሃገራዊ ለውጥ” በሚል መሪ ቃል የ2011 ዓ.ም የክረምት ወራት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት በወጣቶችና ስፖርት ኮምሽን እና በወጣቶች ፌዴሬሽን አስተባባሪነት ይካሄዳል፡፡

የበጋ ወራት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ሲያበረክቱ ለቆዩ ወጣቶች የአስተዳደሩ ወጣቶችና ስፖርት ኮምሽን የምስጋና ሰርተፊኬት አበርክቷል፡፡

በትዕግስት ቶሎሣ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here