የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለ11ኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2ሺ 800 ተማሪዎች አስመረቀ

0
156

የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው የቀሰሙትን እውቀት በመጠቀም ለሀገር እድገትና ብልጽግና እንዲሁም ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡

 

     ዩኒቨርሲቲው በ6 ኮሌጆችና በ41 የትምህርት ክፍሎች ተቀብሎ ያሰለጠናቸውን 2ሺ 800 ተማሪዎች ለ11ኛ ጊዜ በድምቀት አስመርቋል፡፡ በዚሁ ስነ ስርአት ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት በሚኒስቴር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የዲሞክራሲ ስረአት ግንባታ መአከል አስተባባሪ የዩኒቨርስቲው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ፍቃዱ ተሰማ እንደተናገሩት ተመራቂዎች በተለያዩ መስኮች ያገኙትን እውቀት ለሀገር እድገትና ሰላም እንዲሁም ለልማት መጎልበት ሊያውሉት እንደሚገባ ነው የገለጹት፡፡

     የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ያሬድ ማሞ በበኩላቸው ሀገር ልታድግና ልትለወጥ የምትችለው በልጆችዋ ህብረትና አንድነት ነው ያሉ ሲሆን  ተመራቂዎችም ይህን ህብረታችንን ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱትን በአንድነት በመዋጋትና ብዘሀነትን አክብሮ ሳይማር ያስተማረን ማህበረሰብ በቅንነትና በታማኝነት በማገልገል ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

     በዩኒቨርሲቲው በዘንድሮው አመት 3.99 በማምጣት የዋንጫና ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆነው ተመራቂ ሚኒሊክ ንጉሴንም ሆነ በስነ ስርአቱ ላይ ያነጋገርናቸው ተመራቂ ተመሪዎች እውቀት ክህሎታቸውን ተጠቅመው ሳይማር ያስተማራቸውን ማህበረሰብና አገራቸውን በሰለጠኑበትም  መስክ ለማገልገል መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡

     ተመራቂዎቹ አክለውም ከፍተኛ ትምህርት ተቁዋማት ላይ የሚማሩ ተማሪዎች የየትኛውም ሀይላት የፓለቲካ መጠቀሚያ ከመሆን ተቆጥበው ለአላማቸው ከዳር ለማድረስ ሊሰሩ እንደሚገባ መክረዋል፡፡

     ዩኒቨርሲቲው በምረቃ ስነ ስረዓቱ ላይ በሀገራችን በተለያዩ መሀበራዊ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ወ/ሮ አሰገደች አሰፋና ለክበር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ አበርክተዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here