በአስተዳደሩ ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው አነስተኛ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን በማገዝ ተግባር ላይ ባለሀብቱ ሊሳተፍ ይገባል ተባለ

0
175

ለረጅም አመታት በኖሩበት ድሬዳዋ ላይ ከውትድርና እስከ መንግስት ተቋማት ስራ ያገለገሉት አቶ ፀጋዬ ገለቱ ዛሬን እድሜ ቢጫናቸው ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው አናሳ ሆኖ ቢፈትናቸው ከዳዊት አረጋውያን መጦሪያ ማእከል ተጠግተው በመደገፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት ለረጅም አመታት ሲያሰቃያቸው የነበረውን የጥርስ ህመም ለመታከም አቅሙ ቢሳናቸውም ዛሬ ግን ወገኔ ባሉት የጥርስ ሀኪም ዶ/ር አድማሱ እሳቸውና ጓደኞቻቸው የነፃ ህክምና እድል ተመቻችቶላቸዋል፡፡ ሁሉም በእድሜ የገፉ አረጋውያንንና የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልዶችን የመደገፍ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባና በተደረገላቸው ድጋፍም መደሰታቸውን አቶ ፀጋዬ ገልፀዋል፡፡

 

     የነፃ ህክምና የተደረገላቸው ታካሚዎች እንደሚሉትም ልክ እንደ ዶክተር አድማሱ በጤና መስክ የተሰማሩትን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ከዚህ ተግባር ትምህርት ወስደው በሚሰሩበት ዘርፍ ህብረተሰቡን ቢያገለግሉ መልካም ነው ብለዋል ፡፡

     የግል ባለሀብቱም ሆነ የጤና ባለሙያው አቅሙ በፈቀደ መልኩ በበጎ ፍቃድ ስራ ወገኑን ቢያግዝ መልካም መሆኑን የሚናገሩት የዶ/ር አድማሱ ስፔሻሊስት የጥርስ ህክምና ተቋም ባለቤት ዶ/ር አድማሱ አበበ  ለሌሎች አርአያ በመሆን ኢኮኖሚያዊ አቅማቸው አናሳ የሆኑ ታዳጊዎችንና አረጋውያንን በየዓመቱ የነፃ የጥርስ ህክምና በመስጠት ሙያዊና የዜግነት ግዴታቸውን መወጣት ከጀመሩ ሁለት አመት እንደሆናቸውና ይህን በቀጣይም አቅም በፈቀደ መጠን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡

     ማህበረሰቡ ውስጥ እንደመኖራችን መሰል የበጎ ፍቃድ ስራዎችን በየሙያ ዘርፋችን በመወጣት ሙያዊ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ሲሉም ዶ/ር አድማሱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በእለቱ በነፃ የአፍ ውስጥ ህክምና ከህዳሴ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለመጡ የኢኮኖሚ አቅማቸው አነስተኛ የሆኑ ተማሪዎችና በዳዊት አረጋውያን መርጃ ማዕከል ተጧሪ የሆኑ አረጋውያን በነፃ ህክምናው ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here