በስፋት እየተስተዋለ የሚገኘው የመሬት ወረራን ለመከላከል የአስተዳደሩ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ በትኩረት በመስራት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ

0
451

በድሬዳዋ አስተዳደር በስፋት እየተስተዋለ የሚገኘው የመሬት ወረራን ብሎም በመካነ ህይወት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተ-ክርስቲያን ላይ ተፈፀመ ስለተባለው የመሬት ወረራ ጋር ተያይዞ ያስረዱት የአስተዳደሩ መሬት ልማትና ማኔጅመነት ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ደራራ ሁቃ የመሬት ወረራው በአስተዳደሩ በስፋት እንደሚስተዋልና ይህንንም ተከትሎ በቤተ-ክርስቲያኑ ላይም የመሬት ወረራው እንደተፈፀመና በቤተ-ክርስቲያኑ ዙሪያ ሰፍረው ለሚገኙ ግለሰቦች በአጭር ጊዜ ውስጥ ምትክ ቦታ በመስጠት ዳግም መሰል የመሬት ወረራዎች እንዳይከሰቱ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡

 

ዶክተር ደራራ አክለውም በከተማ አስተዳደሩ በህገ-ወጥ የመሬት ወረራ ከአስራ አምስት ሺህ እስከ ሃያ ሺህ የሚገመቱ ቤቶች እንደተገነቡና በቀጣይም በህገ-ወጥ መንገድ የተገነቡ ቤቶችን ብሎም በህገ-ወጥ መንገድ የሚካሄዱትን የመሬት ወረራዎች ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተለያዩ ጥናቶችን በማካሄድ ወደ እርምጃ እንደሚገባም ነው የገለፁት፡፡

መጋቢት 11 ቀን 2011 ዓ/ም በድሬዳዋ መካነ ህይወት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተ-ክርስቲያን ከመሬት ወረራ ጋር ተያይዞ ተፈጥሮ በነበረው ሁከትና ግጭት የአስተዳደሩ ፖሊስ ተሳታፊ ነበሩ ያላቸውን 7 ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር ማዋሉን የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ዲቪዥን ሀላፊ ዋና ሳጅን ባንታለም ግርማ ገልፀው ችግሩ ዳግመኛ እንዳይከሰት የአስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን ከፌደራል ፖሊስና ከመከላከያ ጋር በጋራ በመሆን በቤተ-ክርስቲያኑ ዙሪያ ተገቢውን የፀጥታና የህግ የማስከበር ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here