በመንግስት ንብረት አያያዝና አወጋገድ ላይ ብክነት ይስተዋላል ተባለ

0
407

በድሬዳዋ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ስር ከሚገኙ ተቋማት መካከል የፅዳትና ውበት ኤጀንሲና የመንገዶች ባለስልጣን  በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ እንዲሁም ከአስተዳደሩ ቋሚ ኮሚቴዎችና የስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ከተውጣጡ አካላት ጋር በንብረት አወጋገድ እና አያያዝ ዙሪያ በተቋማት ላይ ድንገተኛ ምልከታ አካሂዷል፡፡

 

     በምልከታውም የከተማውን ፅዳትና ውበት የመጠበቅ ኃላፊነት የተጣለበትን የፅዳትና ውበት ኤጀንሲ ምቹ ባልሆነ በቆሻሻ ክምር በተጣበበ ቅጥር ግቢው ለረጅም አመታት ባለቤት አልባ ሆነው መወገድ ሲገባቸው ባልተወገዱ ተሽከርካሪዎችና የአገልግሎት ያለአግባብ በጠባብ መጋዘን በተከማቹ ቁሳቁሶች መሞላታቸውን ለመታዘብ ተችሏል፡፡

       ሌላው በከተማው ለረጅም አመታት ጥገና የሚያስፈልጋቸውን መንገዶች ለመጠገን የቅርጣን እጥረት እንደ ምክንያት ሰበብ ተደርጎ በመንገዶች ባለስልጣን መስሪያ ቤት ወሳኝ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን የቅርጣን በርሜሎች ለግንባታ ግብዓት ሊሆኑ በሚገባቸው ብረታ ብረቶችና በጥቂት በጀት ተጠግነው አገልግሎት መስጠት በሚችሉ የመንገድ ጥገና ማሽነሪዎች ግቢውና መጋዘኑ ተገንብቶ ለመመልከት ተችሏል፡፡

      ይህንንና መሰል ችግሮችን የሁሉም ተቋማት ችግር መሆኑን የገለፁት የአስተዳደሩ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱልጣን አሊዬ ተቋማቱ ንብረቶችን ለተለየ ግልጋሎት በአግባቡ ከመጠቀም በዘለለ በሽያጭና በተለያዩ መንገዶች ሊወገዱ የሚገባቸውን ንብረቶች በግዢና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በማስተላለፍ ጥገና የሚገባቸውን ንብረቶች ጥገና በማድረግ ወደ ስራ ማስገባት እንደሚገባቸው አሣስበው በቀጣይ በዚህ ተግባር ላይ ተሰማርተው በሚገኙ ተቋማትና ኃላፊዎች ላይ የተጠያቂነት እርምጃ እንደተቋም ይወሰዳልም ብለዋል፡፡

    አቶ ሱልጣን አክለውም በቢሮ ደረጃ መውሰድ ያለብንን እርምጃ ለመውሰድ በዝግጅት ላይ ነን ሲሉ  ገልፀዋል፡፡ በተመሳሳይም ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስትና የህግ አካላት እዚህ ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩና ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎንም ለተቋማቱ ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ለወደፊት እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

     እኛም በምልከታችን እንደታዘብነው ተቋማቱ በንብረት አያያዝ ረገድ ህዝብና መንግስት የጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ አለመወጣታቸውን ለመመልከት ችለናል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here