የሴቶችን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ ተሳትፎ ተጠቃሚት ከፍ ለማድረግ ሴቶችን የማብቃት ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የድሬደዋ ኢህአዴግ ሴቶች ሊግ አሰታወቀ፡፡

0
110

የሴቶች ሊግ አራተኛ መደበኛ ጉባኤውን ህዳር 21 እና 22 እንደሚያካሂድ ታውቋል፡፡ ሊጉ የሚያካሂደውን ጉባኤ አስመልክቶ የድሬደዋ ኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ሊቀመንበር ወ/ሮ አይናለም ተዘራ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ሴቶች ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ከማድረግ አንፃር የተከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

በገጠር በተለይ ሴቶች ካሉበት ማህበራዊ ጫና ተላቀው በኢኮኖሚ እራሳቸውን እንዲችሉ ለማድረግ ሰፊ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡

ከሰላምና ፀጥታ መደፍረስ ጋር ተያይዞ ዋንኛ ተጐጂ ሴቶች እንደመሆናቸው ግጭትን በመከላከል ረገድ ሴቶች ቀዳሚ ድርሻ እንዲኖራቸው ሲደረግ መቆየቱን ወ/ሮ አይናለም አብራርተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት እንደ ሃገርም ሴቶች የአመራርና የውሳኔ ሰጪ አካል እንዲሆኑ እየተደረገ እንደመሆኑ በድሬደዋ ይህ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይደረጋል ብለዋል፡፡ ወ/ሮ አይናለም ሊጉ የሴቶችን በራስ መተማመን በማዳበር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ይሰጣል ተብሎ የታመነበት የጀግኒት ፕሮግራምን ጨምሮ ሌሎች ሴቶችን የሚመለከቱ መርሃ ግብሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ሊቀመንበራ ጠቁመዋል፡፡

በአጠቃላይ ህዳር 21እና 22 በሚካሄደው የሊጉ መደበኛ ጉባኤ ባለፉት ሁለት አመት ተኩል የተከናወኑ ተግባራት እንደሚገመገሙ ተገልጿል፡፡ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡

በጉባኤው ከሁለት መቶ አርባ በላይ ሴቶች ይሳተፋሉ፡፡ የፌድራልና የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ሴቶች ሊግ ጨምሮ የሁሉም ብሄራዊ ድርጅቶች በጉባኤው መክፈቻ ተገኝተው ድጋፍና የአጋርነት ንግግር ያደርጋሉ የድሬደዋ ኢህአዲግ ሴቶች ሊግ አዲስ ሊቀ መንበር ምርጫ እንደሚካሄድ ታውቂል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here