በድሬዳዋ በተለያዩ ጊዜያት የሚከሰቱትን ግጭቶች ለመፍታት በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ አካላትን ማወያየት በአስተዳደሩ እየተካሄደ ነው

0
136

በዛሬው እለትም በመንግስት ተቋማት የሚገኙ የስድቱ ፓርቲዎች አባላት የአስተዳደሩ ከንቲባ ኢብራሂም ኡስማን ፣የኢ.ህ.አ.ድ.ግ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሽመልስ ከበደ ና ሶ.ዴ.ፓ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልሰላም አህመድ እንዲሁም የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱም በአስተዳደሩ በተወሰኑ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶች የብሄር ግጭት በማስመሰል የራሳቸውን ጥቅምና ፍላጎት ለማሳካት የሚሯሯጡ ግለሰቦችና አመራሮች የሚያደርጉት መሆኑ በውይይቱ የተነሳ ሲሆን ይህንን ከስር መሰረቱ ለማድረቅ አባላቱ የድርሻቸውን በመወጣት የህብረተሰቡን ሰላም ለማስጠበቅ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡም በውይይቱ ተነስቷል፡፡

ባለፉት ጊዜያት የተከሰቱትን ግጭቶች መንስኤና በቀጣይ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እየተናፈሰ ያለው የይገባኛል ጥያቄ የሁለቱ መንግስታትና ድርጅቶች አቋም አለመሆኑ ፣የህግ የበላይነት ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና የኢ.ህ.አ.ድ እና የአጋር ድርጅቶች ማንኛውም አባል በግጭትና በሁከት ውስጥ ተሳትፎ ቢገኝ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ በአቋሞች ላይ ውይይት አካሄደዋል፡፡

በቀጣይም በአቅጣጫ የተቀመጡትን በመተግበር የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ አጥፊዎችን የማጋለጥና በአስተዳደሩ የህብረተሰቡ ሰላም የማስጠበቅ ኃላፊነታቸውን አንደሚወጡ በውይይት መደረኩ የተሳተፉ የድርጅት አባላት ተናግረዋል ፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here