በድሬደዋ የተወሰኑ አካባቢዎች የተከሠተው ግጭት የብሄር ግጭት እንዳልሆነ ተገለፀ

0
358

የድሬደዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒከሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት ከህዳር 8/2011 ዓ.ም ጀምሮ በከተማዋ የተወሰኑ አካባቢዎች በተፈጠረ ግጭት በሰው ህይወት፣ በአካልና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ገልፀዋል፡፡

በኃላፊ ገለፃ በተፈጠረው ግጭትም በመጋላ ጨብጡ በተባለ አካባቢ የአንድ ሰው ህይወት

አልፏል ፣ አራት መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል በተመሳሳይም በመልካ ጀብዱ ከቀጠና አንድ እስከ አራት ባሉ

አካባቢዎች እና በመጋላ በተከሰተ ግጭት 2 ግለሰቦች በሁለት ታጣቂ ሚኒሻ አካላት በተተኮሰ ጥይት

ሲቆስሉ ሁለት የጸጥታ አካላትም በተወረወረ ድንጋይ ጉዳት እንደደረሰባቸም ተገልጻል::

ከዚህም ጋር በተያያዘ በመልካ ጀብዱ በነበረ ግጭትም በሁለት ቤቶች እና በአንድ አጥር ላይ የቃጠሎ አደጋ መድረሱንና በግጥቱ በተቃጠሉት ቤቶች ንብረት የሌላቸው ባዶ እንደነበሩ የንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ በሠጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መገንዘብ ተችሏል፡፡

በቀበሌ 07፣09 መንገድ የመዝጋትም ቤቶች ላይ በቀለም ምልክት የማድረግ እንዲሁም በድሬደዋ ዩኒቨርስቲ አካባቢዎች መጠነኛ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች የነበሩ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው አመራሮችና በፀጥታ ሀይሎች ጥረትና በአካባቢው በሚኖሩ ማህበረሰቦች ጋር በተደረገ ውይይት ችግሩን መፍታት መቻሉን ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

በግጭቱ ተጠርጣሪ የሆኑ 147 ሰዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የገለፁት ኃላፊው የተፋጠረውን ግጭት በህዝብ መሐል የተፈጠረ የብሔር ግጭት ለማስመሰል የሚሰሩና የተለያየ አጀንዳ ይዘው በተደራጀ መልኩ በድሬደዋ የከፋ ትርምስ ለመፍጠር የሚፈልጉ ሀይሎች ቢኖሩም የከተማው ነዋሪ አበሮ የኖረ ሰላም ወዳድ ሕዝብ በመሆኑ የታሰበው ሊሳካ አለመቻሉን አስረድተዋል፡፡

በተደጎጋሚ ግጭት በሚከሰትባቸው የከተማዋ አካባቢዎች የፀጥታ ሀይል በቋሚነት ተመድቦል እንዲሁም ለግጭቱ መፈጠር ምከንያት የሆኑ በግህ የሚጠየቁበት አሠራር መፈጠሩን የገለፁት ኃላፊው ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር እንዲተባበር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በቀጣይ የከተማዋን ሠላም በዘላቂነት ለማስጠበቅ በተለያየ ደረጃ ነዋሪዎች ጋር ሰፊ የውይይት መድረክ እንደሚዘጋጅ ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here