በድሬደዋ አስተዳደር በትላንትናው ዕለትም በተወሰኑ ቀበሌዎች ግጭት እንደነበር ተገለፀ

0
309

ባለፉት ቀናት በድሬደዋ የተከሠተው ግጭትበ12/2011ዓ.ም ዕለትም በቀበሌ 06፣07፣08፣09 ከምሽት 1 ሠዓት እስከ ምሽቱ 5 ድረስ የቆየ መንገድ መዝጋት ውከት እንደነበር የአስተዳደሩ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ ገልፀዋል፡፡

ከምሽቱ አንድ ሠአት በተጀመረው ግጭትም የአንድ ሰው ህይወት ማለፍንና አንድ ሰው ከባድ አደጋ ደርሶበት በድል ጮራ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኝ ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

በለገሀሬ አንድ ቤት ከንብረት ጋር የተቃጠለ ሲሆን በግጭቱም ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እንዳሉና በ06 ቀበሌ አካባቢዎች ከስጋት የተነሳ የንግድ ቤቶች የተዘጉበት ሁኔታ እንዳለ ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

በግጭቱም የድንጋይ ውርወራ፣ ስለታማ የሆኑ መሳሪያዎች እንዲሁም የጥይት ቶክስ ልውውጥ ጉዳት እያደረሰ ስለሆነ ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካሉ ጋር በጋራ በመሰራት እያደረሱ ያሉ ግጭቶችን ለማስቆም የእርስ በርስ ውይይት በማድረግ ሰላማቸውን የማስጠበቅ ኃላፊነታቸውን መወጣት አለባቸውም ብለዋል፡፡

በአስተዳደሩ በቂ የፀጥታ ሀይል በመኖሩ ማህበረሰቡ ከስጋት ነፃ በመሆን ችግር በሚፈጠርባቸው አካባቢዎች ለፀጥታ አካላት መጠቆም እና ወንጀለኞች ለህግ አሳልፎ የመስት ሃለፊነታቸውን እንዲወጡም ኃላፊው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here