የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ውይይት ተጠናቀቀ

0
336

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ስልጠና ፍኖተ-ካርታ የጥናት ውጤት ግብዓት ማሰባሰቢያ ውይይት መድረክ በተቋሙ የአስተዳደር ሰራተኞች እና በመምህራን ሰፊ ውይይት ተደርጎበት ተጠናቀቀ፡፡

             ከመስከረም 28-30/2011 ዓ.ም ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሚካሄደው የፍኖተ-ካርታ ውይይት የትምህርት ጥራትና ፍታዊ የትምህርት አሰጣጥ እንዲሁም የነበረው የትምህርት አሰጣጥ ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎል ፡፡

በዩኒቨርሲቲው የማነጅመንት ክፍል መምህር ምክሬ ፍቃዱ በሰጠው አስተያየት የትምህርት ጥራት ከግዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ ሄዶ አጠያያቂ ሁኔታ ላይ በመድረሱ መንግስት ይህንን ችግር ለመፍታት ፍኖተ ካርታ ማዘጋጀቱ የትምህርቱን ጥራት ከወደቀበት ለማንሳት ትኩረት መሰጠቱን ያመላክታል በማለት በፍኖተ ካርታው ባደረጉት ውይይትም ግብአት የሚሆኑ ሀሳቦችን ማቅረባቸውንም ገልፀዋል፡፡

መምህር ምክረ አክለውም የትምህርት ተቋማትና የመምህራን የሙያ ማህበራት ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነትን ነፃ በመሆን ከመምህራን ምልመላ እስከ ደረጃ እድገት የነበሩትን ችግሮች በፍኖተ ካርታው አቅጣጫ መቀመጡ የትምህርቱን ጥራት ወደሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በእንግሊዘኛ ትምህርት ክፍል በረዳት ፕሮፊሰር ማአረግ መምህርና በየኒቨርስቲው የተከታታይና እርቀት ትምህርት ዳሬክተር ደሳለኝ ዋቅጅራ እንደተናገሩት ትምህርት ለአንድ አገር እድገት የአንበሳውን ድርሻ የያዘ በመሆኑ ለማህበራዊ ፣ለኢኮኖሚውና ለፖሎቲካው መሰረት ነው፡፡የተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ ሂደቱን የጠበቀና ማህበረሰቡን ተደራሽ ያደረገ ነውም ብለዋል፡፡

        የትምህርት ጥራትን ከግብ ለማድረስ መምህራን፣ ተማሬዎች፣ህብረተሰቡና መንግስት የዚህ ሁሉ ድምር ነው ይህ በመሆኑ ከዚህ በፊት በነበሩ ካሪኩለም ቀረፃው ከላይ እስከታች አሳታፊ ተደርጉ አግባብነት የተፈጠረ ባለመሆኑ ችግሮችን ተመልክተናል አሁን ላይ ፍኖተ ካርታው መዘጋጀቱ በፍጥነት ወደ ስራ ያስገባናል ብለዋል ፡፡

       ዩነኒቨርስቲው በሦስተኛ ቀን ውሎአቸውም የ2010 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ላይ እና በ2011 ዓ.ም እቅድ ግቦች ላይ ከእስተዳደሩ ሰራተኞችና ከመምህራን ጋር ሰፊ ውይይት አድርጓል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here