በመብራት እና በይዞታ ይገባኛል ጥያቂ ምክንያት የንፁህ መጠጥ ውሀ ፕሮጀክት አለመጠናቀቁ ተገለፀ፡፡

0
374

በአለም ባንክ ድጋፍና በአስተዳደሩ ወጪ ከ5 ዓመት በፊት ስራው የተጀመረው የንፁ መጠጥ ውሀ ፕሮጀክት በመስከረም ወር ወደ ስራ ይገባል ቢባልብ በመብራትና በይዞታ ይገባኛል ችግር ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ስራው መራዘሙ ተገለፀ፡፡የአስተዳደሩ ከንቲባና ከፍተኛ አመራሮች ጨምሮ ፕሮጀክቱን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

 ከአለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ እና በአስተዳደሩ ወጪ ሰባት መቶ ሚሊየን ብር በጀት የተያዘለት ይህ ፕሮጀክት የንፁህ መጠጥ ውሀ ጉድጓዶችን የመቆፈሩ ስራ ከ5 ዓመት በፊት መጀመሩ ይታወሳል፡፡እነዚህ ጉድጓዶች ወደ ስራ ሲገቡ 11ሺህ ሜትር ኩብ ውሀን በማመንጨት የድሬደዋን የንፁህ መጠጥ ውሀ ችግር አንደሚቀርፉ ታምኖበት ነበር ነገር ግን ፕሮጀክቱ ከማስፈፀም አቅም ማነስ ፣ከመብራት አለመዘርጋት፣ የይዞታ ይገባኛል ጥያቄ ነፃ አለመሆንና ከፕሮጀክቱ ውስብስብ ከመሆን የተነሳ አንድ አመት ተኩል መጓተቱን የድሬደዋ ውሀና ፍሳሽ ኃላፊ አቶ መሀመድ መሴ ገልፀዋል ፡፡

     ፕሮጀክቱ ከዚህ በሀላ እንዳይጓተትና አስተዳደሩ ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጠው የአስተዳደሩ ከንቲባና የተለያዩ የአስተዳደሩ አመራሮችን ጨምሮ ጉብኝት ማስፈለጉ ያሉትን ችግሮች በመመልከት ሁሉም የድርሻቸውን ኃላፊነት በመወጣት ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ ኃላፊው ጨምረው ተናግረዋል ፡፡

       ኃላፊው አክለውም በቶሚ ያለው የውሀ ፕሮጀክት ሙሉበሙሉ ባይሆንም በከፊል የሙከራ ስርጭት መጀመሩን በመግለፅ ፕሮጀክቱን ሙሉበሙሉ ወደ ስራ ለማስገባት በትኩረት አንደሚሰሩና ህብረተሰቡ እንዲታገሳቸው ጠይቀው በጎሮ የሚገኘውን ሪዘርቨየር እስከ ጥቅምት 15/2011 በተወሰነ መስመር ወደስራ እንደሚገባም ቃል ገብተዋል፡

     በጉብኝቱ ማጠናቀቂያም የአስተደደሩ ከንቲባ አቶ ኢብራሂም ኡሱማን እንደተናገሩት በጉብኝቱ ከመሬት ይዞታ ጋር በተያያዘ የተመለከቱትን ችግር ውሳኔ በመስጠት በአፋጣኝ ወደ ስራ እንደሚገባና የመብራት ችግር እስከሚፈታ ጂኔተሮችን በአማራጭነት እንደሚጠቀሙ በመግለፅ ከሁለት ወር በኃላ ያሉ ችግሮችን በመፍታት በድሬደዋ ያለው የውሃ ችግር ሙሉለሙሉ እንደሚፈታ ተናግረዋል ፡፡

     ከኒቲባው አክለውም ፕሮጀክቱን የሚመሩ አካላት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚነሱ ቅሬታዎችን በአግባቡ አሟጠው መፍትሄ ለመስጠት   በቁርጠኝነት በመስራት የህብረተሰቡን የመጠጥ ውሀ ችግርም እንዲፈቱ አሳስበዋል፡፡

   በሌላ በኩል ከመብራት ጋር የተነሳውን ችግር በተመለከተ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ድሬደዋ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍቅረማሬያም አለማየሁ ችግሩ እንደለ አምነው ክፊተቱ ከግዥና ከዶላር ምንዛሬ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይ መስሪያ ቤታቸው አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ተገቢውን ትኩረት እንደሚያደርግ አቶ ፍቅረማሬያም ጨምረው ገልፀዋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here