በአሰተዳደሩ 11 ኛው የሰንደቅ አላማ ቀን በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ተከብሯል፡፡

0
319

በዓሉን አስመልክቶ በተካሄደው የፓናል ውይይት ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ የህረተሰብ ክፍሎች በበአሉ ላይ ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ሰንደቅ አላማ የታሪክና የማንነታችን መገለጫ በመሆኑ አስፈላጊውን ክብር ሁሉ መስጠት እንደሚገባም ነው ተሳታፊዎቹ በውይይቱ የገለፁት፡፡

ወጣቱ በተለይም ለሰንደቅ አላማ ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ የጠራ አመለካከት እንዲይዝ መንግስት በትኩረት መስራት አለበት ሲል የውይይቱ ተሳታፊዎች በአፅኖት ተናግረዋል፡፡

የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ አብዱሰላም መሐመድ በበኩላቸው የሰንደቅ አላማ ቀንን ስናከብር ለአገራችን ልማት ቀጣይነት በጋራ ለመስራት ቃል በመግባት ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡ 11 ኛው የሰንደቅ አላማ ቀንበዓል በአሰተዳደሩ በሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ በፌዴራል ተቋማት እንዲሁም በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ሰንደቅ አላማ በመስቀል ስርዓቱ ተጠናቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here