በፍቅር እንደመር በይቅርታ እንሻገር

0
328

እውነተኛ ፍቅር በደልን አይቆጥርም፡፡ እውነተኛ ፍቅር በበጎ ነገር ሁሉ ደስ ይለዋል፤ በክፉ ነገር ግን ደስ አይለውም፡፡ በበደለኝነት ስሜት ራሱን ያራቀውንና ያገለለውን በመውቀስ ሲጸጸት ከልብ ይቅር ብሎ ማቅረብና ማካተት ያስፈልጋል፡፡ ይቅርታ በእውነተኛ ፍቀር ከተሞላ ልብ የሚመነጭኛ የበደለኛ ፍቱን መድኃኒትና የጠብንና የጥፋትን ኃይል ጸጥ የሚያደርግ ነው፡፡

የሀገራችን  ህዝቦች የአብሮነት ታሪካቸው የሚያሳየው ለሰላም፣ ለልማትና ዴሞክራሲ ብሎም ለአገራዊ አንድነት ያላቸው ጽኑ አቋም ምንጊዜም የማይሸረሸር መሆኑ ነው። ይህ እውነታ በቅርቡ በክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በተደረገው የፍቅር፣ የይቅርታና የመደመር ጥሪ ከአገር ውስጥ አልፎ በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ልዩነቶችን ወደ ጎን በመተው ከጫፍ እስከ ጫፍ ለጥሪው  ምላሽ በመስጠት  መላውን ዓለም ያስደመመ ታሪክ ሠርተዋል፡፡

በተለይ አዲሱ አመራር ወደ ስልጣን ከመጣበት ከመጋቢት ወር 2010 ዓ.ም ጀምሮ የፍቅር፣ የመደመርና የይቅርታ ጥሪን በማብሰር በአገር ውስጥና በውጭ ላሉ ኢትዮጵያውያን ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ ባከናወኗቸው ተጨባጭ የለውጥ እንቅስቃሴዎች እነሆ አዲስ ምእራፍ ተከፍቶ የአገሪቱ አውድ በመሰረቱ የተቀየረበት ምእራፍ ላይ ደርሰናል። ባጠቃላይ ከዚህ መማርና መገንዘብ የሚቻለው ፍቅርና ይቅርታ ምን ያህል ኃይል እነዳለው ነው፡፡

ባለፉት አራት ወራት በአገር ውስጥና በውጭካሉት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በፍቅርና በመደመር የጋራ ቤታችን የሆነችውን ኢትዮጵያን ለመገንባት ምቹ ሁኔታ የፈጠረ  ውይይትና ምክክር ተደርጓል። እንዲሁም ከጎረቤት አገራት ጋር በተለይ ከኤርትራ ጋር ታሪካዊ የተባለለትና በሁለቱም አገር ዜጎች መካከል የነበረውን የጥላቻ ግንብ ያፈረሰ ግንኙነት ተመስርቷል።

አሁን  አገሪቱ አስቀድማ  ከነበረችበት ማህብዊ ቀውስ ወጥታ ወደ አዲስ የለውጥ ምእራፍ የተሸጋገረችበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን። በመሆኑም መጪው የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት አቀባበል ስናደርግ መላው ህዝባችን አሁን የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል በአዲስ መንፈስ ለአገር ግንባታ፣ ለዘላቂ ሰላም እና ዋስትና ላለው ዴሞክራሲ ስርዓት መጠናከር ድርሻውን መወጣት በሚያስችል መልኩ ሊሆን ይገባዋል።

ስለሆነም አዲሱን ዓመት ስንቀበልየአስተዳደራችን ማህበረሰብ  ይህን  መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ጥሩ መስተጋብር በመፍጠር ለጋራ ጥቅምና እድገት ተደምረው ይበልጥ አንድነታቸውንና አብሮነታቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል፡፡

ስለሆነም አሁን የተጀመረው የፍቅር፣ የይቅርታና የመደመር ጉዞይበልጥ ለማጎልበት ጳጉሜ 02/2010 ዓ.ም “አዲሱን ዓመት በአዲስ መንፈስ” አቀባበል ለማድረግ ለመላው ህዝባችን መልእክት የሚተላለፍበትልዩ ዝግጅት ለማካሄድ ታቅዷል። እርስዎም የዚህ ሀገራዊ አጀንዳ አካልና ባለቤት እንዲሆኑ በክብር ተጋብዘዋል፡፡

  የመንግስት ኮዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

ድሬደዋ

                               28/12/2010ዓም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here