ለሠላማችን ይህ ነው ተብሎ የማይገመት ትልቅ ዋጋ ተከፍሎበታል

0
309

እኛ ኢትዮጵያዊያን የእርስ በእርስ ግጭትንና ጦረነትን የምናውቀው በወሬና በሚዲያዎች ብቻ አይደለም፡፡ በተግባርም እንዳሳለፍነው የእርስ በእርስ ግጭቱና ጦርነቱ ብዙ ነገር አሳጥቶናል፡፡ ለዚህ ደግሞ ችግሩ ያላነኳኳው ቤት ያለሞኖሩን መጥቀስ ብቻ በቂ ነው፡፡ አኛ ግጭትንና ጦርነትን የምናውቀው በተግባር በተጨፈጨፉ ህጻናት፣ ወጣቶች፣ አረጋውያንና እናቶችም ጭምር ነው፡፡  በብዙዎቻችን ቤት ዛሬም ድረስ አሻራው አለ፡፡ በሀገር ደረጃም ለድህነታችንና ለኋላ ቀርነታችን ዋናው መንስኤ ይኸው ማባሪያ ያልነበረው የእርስ በእርስና የውጭ ግጭት ነበር፡፡

ይህ ወቅት ለወዳጆቻችን መልካም የምስራች ሲሆን ለጠላቶቻችን ግን የመርዶ ያህል እንቅልፍ የሚያሳጣ ነው፡፡

 

                በተፈጠረው በዚህ ሠላም ልማትን የሞት ሽረት ጉዳይ አድርገን ቀጣዮቹ የጋራ ጠላቶቻችን ድህነትና ኋላ ቀርነት መሆናቸውን በደረስንበት የጋራ መግባባት መሠረት በነዚህ በሁለቱ ቀንደኛ ጠላቶቻችን ላይ መጠነ ሰፊ ዘመቻ ከፍተናል፡፡ የማንንም እጅ ሳናይ በራሳችን አቅም ከድህንትና ኋላ ቀርነት ለመላቀቅና የአስተዳደራችንን በሎም የሀገራችንን ህዳሴ ለማረጋገጥ ከጫፍ እስከ ጫፍ ሆ ብለን በቁጭት የተነሳንብት ወቅት ላይ ደርሰናል፡፡ የህዳሴያችንን አይቀሬነት የምናረጋግጥበትና የይቻላል ዓርማችን የሆነው ታላቁ የህዳሴው ግድባችን ሊጠናቀቅ በደጅ ነው፡፡                 በተለይ ፊታቸውን ወደ ልማቱ በማዞር ለህዝባቸው ጠብ የሚል ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ የተሳናቸው የሻዕቢያ መንግሰት እና በዙሪያው የተኮለኮሉት አኩራፊ ኃይሎች ከወጣንብት ከፍታ ሊያወርዱን የሚችሉ እየመሰላቸው ዛሬም ድረስ ምንም የአቋ ም ለውጥ አይታይባቸውም፡፡ ምክኒያቱም ህዝባቸው የሚያነሳውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጠያቄ አቅጣጫ ለማስቀየርና የህዝባቸውን ትኩረት ለመቀልብስ ብቸኛ አማራጭ አድረገው የተያያዙት የአካባቢውን ሠላም በማተራመስ ቀጠናውን  የእልቂትና የብተና ማድረግ ነው፡፡

                 ጥቂት መዘናጋት ትልቅ ጥፋት ሊያደርስ ስለሚችል ለሠላማችን ሁላችንም በንቃት ዘብ ልንቆም ይገባል፡፡ በተለይ ነዋሪው በዕለት ተዕለት የኑሮ እንቅስቃሴው ሠላማችንን ሊያደፈርሱ የሚሽሎከለኩ፤ ዕኩይ ተልዕኮ አንግበው የተነሱ ኃይሎችን በንቃት ከመከታተል ጀምሮ ወጣቶች የእነሱ መጠቀሚያና ሰለባ እንዳይሆኑ እስከ መምከር ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል፡፡

የመንግስትኮሙዩኒኬሽንጉዳዮችቢሮ

                                                                                      ድሬዳዋ

                               9/12/2009 .

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here