ሠላማችን የህዳሴያችን ዋስትና ነው !!!

0
266

ወቅቱ በጋራ የመልማት ፍላጎታችንን በማቀናጀትና የጋራ ጠላታችን በሆኑት ኋላቀርነትና ድህነት ላይ የከፈትነውን መጠነሰፊ ዘመቻ ከዳር በማድረስ የአገራችንን ህዳሴ ሊቀለበስ ከማይችልበት ደረጃ ለማድረስ ትንፋሻችንን ሰብሰብ አድርገን የሞት ሽረት ትግል የምናደርግበት ነው፡፡ካለፈው የትግል ተሞክሯችን እንደምንገነዘበው ትግላችን መራራና እልህ አስጨራሽ ቢሆንም የድላችን አይቀሬነት ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡

          በልዩነታችን ደምቀንና አጊጠን ልዩነትን ያለገደብ በሚያስተናገደውሕገመንግስታዊ ሥርዓታችን ውስጥያለው ጠንካራ አንድነታችን በርካታ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ተሻግረን ወደህዳሴያችን እየገሰገስን ለምንገኘው ለእኛ ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ የሆነው ህገመንግሰታችን በመፈቃቀድና በመከባበር ለመሠረትናት አዲሲቷ ኢትዮጵያ ሠላም ፣ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና ህዳሴ ፅኑ መሠረት ነው፡፡ ይህ ህገመንግስታችን እስካሁን በሁሉም ዘርፎች  ላስመዘገብናቸውም ሆነ ለወደፊቱ ልናስመዘግባቸው ላሰብናቸው ውጤቶች ፅኑ ዋስትናና መሠረት ከመሆኑም በላይ ክቡር ከሆነው የሰው ልጅ ነፍስ፣ደም፣ ሥጋና አጥንት ዋጋ ተከፈለበትና እልፍ አእላፋት ውድ የህዝብ ልጆች የተሠዉለት፤ ለወደፊቱም የሚሰዉለት ነው፡፡

     እንግዲህ ይህን ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ የሆነውን  ህገመንግስታችንን ልክ እንደ ዓይን በሌናችን ልንጠብቀው፣ ልንንከባከበውና ምንም ሳሸራረፍ ልንተገብረው፤ ብሎም ለትውልድ ልናቆየውና ልንስተላልፈው ይገባል ፡፡ ለዚህ ምክኒያቶቹ  ከላይ የጠቃቀስናቸው ብቻ አይደሉም፡፡ የህገመንግስቱ ባለቤት ማነው የሚለውን መሠረታዊ ጥያቄ በአገራችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በማያሻማ መልኩ የመለሰ ህገመንግስት በመሆኑም ጭምር ነው፡፡ ህገመንግስቱ የብሄር፣የጾታ፣ የሀይማኖትና የእምነት ነጻነት ብሎም እኩልነታቸው የተከበረላቸው የአገራችን ብሔር፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች አንጡራ ሀብታቸው ነው፡፡

       አንዳውም ከምናስበውና ከምንገምተው በላይ አንጡራ ሀብታቸው ብቻ ሳይሆን  ሠላማቸውን የሚጠብቁበት የፍቅር ማሰሪያቸው ነው ፡፡ ስለሆነም መጨበጫ የሌለውን የበሬ ወለደ አሉባልታ ከሚነዙ የከሠሩ ፖለቲከኞችና ሚዲያዎች አኩይ ተልዕኮ ሠላማችንንና ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ የሆነውን ህገመንግስታችንን በጋራ ልንከላከል ይገባል ፡፡

     ከተያያዝነው ፈጣን  የህዳሴ ጉዞ አንዳችም ጉዳይ ሊዘናጋን እንደማይችል ደግመን ደጋግመን የያዝነው አቋማችን ዛሬም የጸና ነው ፡፡

                                                               የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

                                                                       ድሬዳዋ

                                                                9/05/2008ዓ.ም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here