የፀጥታና ሚሊሻ አስተዳደር አብይ የስራ ሂደት

  • የአካባቢው ፀጥታ ለማስከበር የተሰማራውን የሚሊሻ ኃይል የተሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ የሚያስችል ተሀድሶ ስልጠናዎች ይሰጣል፡፡
  • ለህገ-መንግስቱና ለስርዓቱ ታማኝ የሆነና ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን ለማስከበር ቁርጠኛ የሆነ ሚሊሻ አባል ለመፍጠር ይንቀሳቀሳል፡፡
  • የሕብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታ የሚያደፈርሱ ሁኔታዎች ይከታተላል ይጠብቃል፡፡
  • የፀጥታ መረጃ መሰብሰብ ማደራጀትና በመተንተን ለውሳኔ ያቀርባል፡፡
  • የሃይማኖትና እምነት ተቋማት እና ተከታዮችቻቸው መካከል የመከባበርና የመቻቻል እሴቶች በማዳበር መልካም ግንኙነት እንዲረጋገጥ  ያደርጋል፡፡
  • የሃይማኖት እምነትተቋማት መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን ድጋፍና ክትትል  ያደርጋል፡፡